አዕምሮህን አሰራው

እንደ ሰው አዕምሮ ሰነፍ የለም፡፡ ካስተኛቹት መንቃት ፤መነሳት ፤ መስራት ፤ መለወጥ የማይወድ ነገር ቢኖር የሰው ልጅ አዕምሮ ነው፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ፊልም ብትጋብዙት ፤ ካፌ 6 ሰዓት ብታስቀምጡት ፤ኢንተርኔት ላይ ቀኑን ሙሉ ብትጥዱት ፤ ምን አለፋቹ ተነስተህ ዙር ብትሉት የማይደክም ማሽን ነገር ነው፡፡ ግን እስቲ 1 መፅሐፍ እንብብ በሉት ፤ 10 ገጽ ሀሳብህን ጻፍ በሉት ፤ ጠዋት ስፖርት ስራ በሉት፤ ቁጭ ብለህ ስራህን አቅድ በሉት በጣም ሰነፍ ነው፡፡
አዕምሮአችን አረም ማብቀል ይቀለዋል፡፡ ነገር ግን በጥበብ የገፉት ሰዎች ያሸንፉታል…..ማሰብ ፤ መስራት ፤ ብርታትን ያስለምዱታል፡፡ ያን ጊዜ ግን መተኛት አይወድም ፤ አሮጌ ነገር አይፈልግም ፤የለውጥ ረሀብተኛ ይሆናል፤መስራት ሲጀምር፤ ሰርተን እስካልጨረስን ድረስ እኛኑ እረፍት ይነሳናል። ማንበብ አዕምሮን ያዳብራል፣ ንቃተህሊናን ያሳድጋል፣ የተሻለ ሰው ያደርጋናል።

Related Articles

ልምዳችንን እንፈትሽ!

የትኛውም ልምድ እስኪጀመር ይከብዳል። ንባብም እንዲያነው ከዚያማ ተፈጥሮን እስኪያሽር ይፀናል። ስለዚህ ወስን። በየቀኑ የምትወስናቸው ትናንሽ ውሳኔዎች የነገ መድረሻህን ይወስኑታል። ማንበብ ውሳኔ ነው፤ ስፖርት መስራት ውሳኔ…

እንዲህ አነባለሁ!

እንዲህ አነባለሁ! • በራእዬ እና በምከታተለው ዓላማዬ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ! • የእኔን፣ የቤተሰቤን፣ የንግዴን፣ የመስሪያ ቤቴንና የሃገሬን ሁኔታ በሚያሻሽል ርእስ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ! • ያነበብኩትን…

ማንበብን መውደድ ተማሩ

ማንበብን መውደድ ተማሩ፡ መጽሐፍ ማንበብ ከየትኛውም ደስታ በላይ ነው; ማንም ሰው በምድር ላይ ሊያሳልፍ ከሚገባው በጣም ከፍተኛ-ውሳኔዎችአንዱ ንባብ መውደድ ነው። ትኩረትን በሚከፋፍሉ ነገሮች በተሞላ፣በየጊዜው በሚለዋወጠው ዓለም መጻሕፍት ጊዜ የማይሽራቸው የእውቀት፣ የጥበብ እና…

Responses