ማንበቤ ብርሀን ሆኖኛል

ለንባብ የሰጠሁት ጊዜ ከመባከን ታድጎኛል። ማንበቤ የትላንት ንግግሬ ከዛሬ ተግባሬ እንዲሰምርልኝ፤ ቃላቶቼ ሀሳቤን እንዲሸከሙልኝ፣ የልብ ዓይኖቼ አርቀው እንዲያዩልኝ፣ ክፉንና ደጉን ፣ ተንኮልና ጥፋቱን እንዲለዩልኝ ብርሀን ሆኖኛል። በማንበቤ ልቤ ሰፊ ሆኖልኛል፣ ሲዋሹኝ፣ሲያሞኙኝ ይታወቀኛል፤ ሲገፋኝ እንዳልንገዳገድ፣ ሲጥሉኝ እንዳልወድቅ ትከሻዬን አስፍቶ ክንዴን አጠንክሮ፣ ሀይልን አላብሶ፣ መንፈሴን አበርትቶልኛል። ማንበቤ በመጠን መኖርን፣ በልክ መናገርን፣ በሚዛን መስፈርን፣ ለክቶ መቁረጥን አድሎኛል።

Related Articles

የህይወታችን መዓዛ

ማንበብ ለህይወታችን የሚሰጠው መዓዛ፣ የሚፈጥርልን ልዩ ስሜት፣ የሚያጎናፅፈን ነፃነት በቃላት ተሰፍሮ የሚያልቅ አይደለም። መፀሀፍት በየትኛውም ደብዛዛ ዘመን ጊዜን የማፍካት ጉልበት ያላቸው፤የህይወት ቅመም ናቸዉ። ማንበብ አንድ ከሚበራ ሻማ ላይ ወደ ሌላ ቁራጭ ሻማ ብርሀን ቢለኮስ፤ ሲበራ የነበረዉ ሻማ እንደማይጠፋ ሁሉ፤ አንባቢ ደግሞ ከንባቡ ያገኘውን እዉቀት በማካፈል በሌላ ሰዉ ህይወት ዉሰጥ የሚበራ ሻማ እንዲሆን ሀይልን ያቀዳጃል። እኛም ከበዛብን የስራ ጫና፣ ከሚፈታተነን የህይወት አዙሪት…

ፍቅር የያዘኝ

ባለቤቴን በጣም እወዳታለሁ፣ ለህይወቴ ትርጉም የሰጠቻት እሷ ናት። እኔ ግን ሌላ ፍቅረኛ አለችኝ።ከሷ ጋር ስሆን ባለቤቴ ደስ አይላትም፣ ጊዜዋን የምሻማበት ስለሚመስላት ግንኙነታችንን አትወደውም። እኔ ደሞ…

እንደ ፍቅር ያለ አስተማማኝ ጥላ የለም

በፍቅር መኖር እረፍት ይሰጣል። ማጣትን ያስረሳል። ፍቅር ያለው ባለው ነገር ይረካል ፣ባለው ነገር ሌሎችን ያገለግላል፡፡ኑሮዬ ይበቃኛልን ያውቃል። በፍቅር የሚኖር የትላንት ማንነቱን አይረሳም፣ ዋጋ የከፈሉለትን ባለውለታዎቹን…

Responses