እንዲህ አነባለሁ!

እንዲህ አነባለሁ!
• በራእዬ እና በምከታተለው ዓላማዬ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ!
• የእኔን፣ የቤተሰቤን፣ የንግዴን፣ የመስሪያ ቤቴንና የሃገሬን ሁኔታ በሚያሻሽል ርእስ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ!
• ያነበብኩትን ወደ ተግባር ለመለወጥ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ!
• ለውጥ ጊዜ እንደሚፈልግ ስለማውቅ የጀመርኩትን የለውጥ መንገድ በቀላሉ የማቆም ሰው አይደለሁም!
• አነባለሁ! አድጋለሁ! እለወጣለሁ! ከራሴ አልፌ ለሌላው እተርፋለሁ!
ለእኔ ማንበብ ከተፈጥሮ እና ከእራሴ የማደርገው እልህ አስጨራሽ ትግል ነው። የማነበውከዘፈቀደ ወደ ፈቃድ (will power) ለመሸጋገር ነው። ፈቃዳችን በሚገባ መመራት የሚችለው ስሜቶቻችን በንባብ ልምድ ሲዳብሩና መገራት ሲችሉ ነው። አንብቡ፣ ፈቃዳችሁን ከዘፈቀደ ወደ ፈቃድ ጠቅልሉት ከዚያም ብርሃናችሁ ለእናንተና ለማህበረሰቡ ይበራል።
ማንበብ እወዳለሁ። ብዙ ሰዎች እንዲያነቡ መምከር ብችል ደስ ይለኝ ነበር።በመጽሐፍ ውስጥ ፍፁም አዲስ የሆነ ዓለም ታገኛለህ።ዓለምን ለመዞር አቅም ብታጣ በማንበብ በምናብህ መጓዝ ትችላለህ። የፈለከው ድረስ ማየት፤ ያሻህ ድረስ መጓዝ ትችላለህ” ማይክል ጃክሰን በአንድ ወቅት የተናገረው ነው። መጻሕፍት የጥበብና የአእምሮ መዝገብ ናቸው፤ አእምሮም የነፍስ መኖሪያ ቦታ ናት፤ነፍስም የማስተዋል ኃይል ናት፡፡ ሰው ሁሉም ክብር ሥጋዊና ክብር መንፈሳዊ የሚያገኘው በአእምሮና በጥበብ ነው፡፡ …ጥበብ እንግዳ በመሆን ጊዜ ወዳጅ ጓደኛ ናት፤ በዐደባባይም ግርማ ሞገስ ናት፡፡

Related Articles

በቀላል አልተገነባም!!!!

በንባብ ያዳበርኩት፣ በምክርም ያጸናኹት እውቀት እንዲሁ በቀላል የገነባሁት ልምምድ አይደለም። ለእኔ  ስነልቦና መገንባት፣ ለነገሮች ያለኝ ክብደት ሚዛኑን የጠበቀ ያልተጋነነና ያልተዛባ እንዲሆን ማድረግ የቻልኩት፣ የሰዎችን ልክ ማወቄ፣ የራሴንም…

Responses