መፅሀፍ ማንበብ የማስተዋል፣ የጥበብ እና የደስተኛ ህይወትህ ምንጭ ነው።

መፅሀፍ አለማንበብ ምን ያህል ጥቅም እንዳሳጠ የምታውቀው መፅሀፍ አንብበህ ያገኘኸውን ጥቅም ስታውቅ ነው። የማያነብ ሰው ለራሱ ባይተወር ነው። 

የማያነብ ሰው ህይወት በሚባል ፍርድ ቤት የእድሜ ልክ የሰው ሀሳብ እስረኛ፣ የጥላቻ እና ቂም እስረኛ፣ የስሜቶች ባሪያ፣ የአለማገናዘብ ሊቅ፣ የፍርሃት አሰልጣኝ፣ ሰው የማስደሰት ሱሰኛ፣ የድህነት አንበል፣ የዘረኝነት ጎተራ ተብሎ ተፈርዶበት የሚኖር  አሳዛኝ ፍጡር ነው ይባላል። 

በጣም የሚገርመው የማያነብ ሰው ለህይወቱ ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎች መጠየቅ አይችልም፤ የማይጠይቅ ሰው ውስጡ እንኳን አለምን የሚቀይር ሀሳብ ቢኖረውም ያንን ነገር ሳያውቅ ይሞታል። እናም መፅሀፍ ማንበብ ጀምር። 

መፅሀፍ ስታነብ፤ ማንበብህ ህይወትህን መስራት ሲጀምር አስተሳሰብ ይሰፋል፤  ታጋሽ ያደርግሃል፣ ትዕግስተኛ ያደርግሃል ፣ ልበ ሰፊ ያደርግሃል፣ ፈዋሽ ንግግር ከአፍህ ይወጣል፤ ትከሻህን ሰፊ ያደርገዋል፤ ንቆ መተው እና ማለፍ ትችላለህ፤ በማያገባህ አትገባም፤ ፍቅር የልብህ ቋንቋ ይሆናል፣ አጠገብህ ያለውን ወንድምህን እንደ እራስህ መውዳድ ትጀምራለህ፤ የበደሉህን በይቅርታ መተው ትችላለህ፤ ከምንም በላይ ከፈጣሪ ጋር ያለህ ህብረት ጥሩ ሁኔታ ላይ ይሆናል። 

መፅሀፍ ማንበብ የማስተዋል፣ የጥበብ እና የደስተኛ ህይወትህ ምንጭ ነው።

━━━━━━✦✗✦━━━━━━ 

Related Articles

አዕምሮህን አሰራው

እንደ ሰው አዕምሮ ሰነፍ የለም፡፡ ካስተኛቹት መንቃት ፤መነሳት ፤ መስራት ፤ መለወጥ የማይወድ ነገር ቢኖር የሰው ልጅ አዕምሮ ነው፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ፊልም ብትጋብዙት ፤ ካፌ…

ማንበብን መውደድ ተማሩ

ማንበብን መውደድ ተማሩ፡ መጽሐፍ ማንበብ ከየትኛውም ደስታ በላይ ነው; ማንም ሰው በምድር ላይ ሊያሳልፍ ከሚገባው በጣም ከፍተኛ-ውሳኔዎችአንዱ ንባብ መውደድ ነው። ትኩረትን በሚከፋፍሉ ነገሮች በተሞላ፣በየጊዜው በሚለዋወጠው ዓለም መጻሕፍት ጊዜ የማይሽራቸው የእውቀት፣ የጥበብ እና…

ለዚህ ነው ማንበብ የሚያስደስተኝ፣ አንባቢ ሰው የሚያስቅቀናኝ፣ መጽሀፍት የሚያጓጉኝ!!!

አንባቢ ሰው አንባቢ ሲናገር አይደነቃቀፍም፤ ሃሳብ አይነጥፍበትም። እንዲያውም ቃላት ለሃሳቦቹ ይሰግዳሉ። ቋንቋ ይታዘዘዋል። የቃላት ሃብቱ ንግግሩ በጉጉት እንዲደመጥ ይጎተጉታሉ። አንባቢ ሰው ትልቅ የሃሳብ ጎተራ አለው።…

Responses