መፅሀፍ ማንበብ የማስተዋል፣ የጥበብ እና የደስተኛ ህይወትህ ምንጭ ነው።
መፅሀፍ አለማንበብ ምን ያህል ጥቅም እንዳሳጠ የምታውቀው መፅሀፍ አንብበህ ያገኘኸውን ጥቅም ስታውቅ ነው። የማያነብ ሰው ለራሱ ባይተወር ነው።
የማያነብ ሰው ህይወት በሚባል ፍርድ ቤት የእድሜ ልክ የሰው ሀሳብ እስረኛ፣ የጥላቻ እና ቂም እስረኛ፣ የስሜቶች ባሪያ፣ የአለማገናዘብ ሊቅ፣ የፍርሃት አሰልጣኝ፣ ሰው የማስደሰት ሱሰኛ፣ የድህነት አንበል፣ የዘረኝነት ጎተራ ተብሎ ተፈርዶበት የሚኖር አሳዛኝ ፍጡር ነው ይባላል።
በጣም የሚገርመው የማያነብ ሰው ለህይወቱ ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎች መጠየቅ አይችልም፤ የማይጠይቅ ሰው ውስጡ እንኳን አለምን የሚቀይር ሀሳብ ቢኖረውም ያንን ነገር ሳያውቅ ይሞታል። እናም መፅሀፍ ማንበብ ጀምር።
መፅሀፍ ስታነብ፤ ማንበብህ ህይወትህን መስራት ሲጀምር አስተሳሰብ ይሰፋል፤ ታጋሽ ያደርግሃል፣ ትዕግስተኛ ያደርግሃል ፣ ልበ ሰፊ ያደርግሃል፣ ፈዋሽ ንግግር ከአፍህ ይወጣል፤ ትከሻህን ሰፊ ያደርገዋል፤ ንቆ መተው እና ማለፍ ትችላለህ፤ በማያገባህ አትገባም፤ ፍቅር የልብህ ቋንቋ ይሆናል፣ አጠገብህ ያለውን ወንድምህን እንደ እራስህ መውዳድ ትጀምራለህ፤ የበደሉህን በይቅርታ መተው ትችላለህ፤ ከምንም በላይ ከፈጣሪ ጋር ያለህ ህብረት ጥሩ ሁኔታ ላይ ይሆናል።
መፅሀፍ ማንበብ የማስተዋል፣ የጥበብ እና የደስተኛ ህይወትህ ምንጭ ነው።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
Responses