የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ
A Book By - ብላታ መርስዔ ኅዘን ወልደ ቂርቆስ

In Stock
የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ
Available Book Type
|
|
📗Printed
Book Info
Author - ብላታ መርስዔ ኅዘን ወልደ ቂርቆስ
Category - ግለታሪክ
Publisher - AAU Press
Translated Book - No
Language - Amharic
Number of Pages - 455
Book Review
በልጃቸው በአምኃ መርስዔ ኀዘን አዘጋጅነት ተሰናድቶ የቀረበ ይኸንን ዘመን አይሽሬ የታሪክ መጽሐፍ እስካሁን አለማንበቤ በእጅጉ ነው የቆጨኝ።
ታሪክን የሚማሩ እና በታሪክ ላይ ለሚመራመሩ ምሁራን የግድ ሊኖራቸውና ሊያነቡት ከሚገባ ግንባር ቀደም የታሪክ ሰነድ መጽሐፎች ውስጥ ይኸኛው አንደኛው እና እንደ ማጣቀሻም ( Reference ) ሊያገለግል ይችላል።
✒️ መጽሐፉ ከዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ይጀምርና ወደ አቤቶ ዘመነ መንግስት ተሸጋግሮ የንግስት ዘውዲቱን ዘመነ መንግስትን አሳይቶ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴን ዘመነ መንግስት በየዓመቱ የተከናወኑትን ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ ታሪካዊ ክንዋኔዎችን መዝግቦ ያስነብበናል።
✒️ የታሪክ አተራረኩ ፣ የዓመተ ምህረት አያያዙ ፣
በወቅቱ የነበሩ ወረርሽኞችን ፣ የመሳፍንትና ፣ የመኳንንቶችን የፖለቲካ ሽኩቻ ፣ የስልጣን ሹም ሽሮችን ተዓማኒነት ባለው መልኩ ሰንዶ ማቅረቡ መጽሐፉ እንዲገዝፍ አድርጎታል ብየ አስባለሁ ።
✒️ ከዚ ቀደም ስለ አቤቶ እያሱ ያነበብኳቸው የታሪክ ጽሁፎች አናሳ በመሆናቸው በዚኛው መጽሐፍ ላይ ብዙ ዝርዝር ነገሮችን ላገኝበት ችያለሁ በተለይ የሸዋዎች ፖለቲካ ፐፐፐ 🤔።
✒️ በዘመኑ የነበሩ የእርስ በርስ ጦርነቶች ፣ የስልጣን ፍትጊያዎች ፣የማህበራዊ የፍትህ ስርዓቶች ፣ የግብር አሰባሰብ ሂደቶች ፣ የኦርቶዶክስ ተዋኅዶ የሐይማኖት አባቶች ከቤተ መንግስቱ ጋር ያላቸው ጉርብትና እና ተጽዕኖ ፣ ሙስሊሞች በሀገረመንግስት ግንባታ ላይ በወቅቱ ያላቸው ሚና ምን እንደሚመስል እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ወደ ሀገር ሲገቡ በህዝቡ ዘንድ ያላቸው እይታ ፣ እነዚህንና የተለያዩ የታሪክ ክስተቶችን ማወቅ ከፈለጋችሁ ‛‛ የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ’’ መጽሐፍን የመጀመሪያ ምርጫችሁ ታደርጉ ዘንድ ወንድማዊ ግብዣየ ነው !
Digital/Audio Book Files
Br590.00