ህብር ህይወቴ

A Book By - ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ

In Stock

ህብር ህይወቴ

Available Book Type

|

|

📗Printed

Book Info

Author - ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ

Translated Book - No

Language - Amharic

Book Review

ህብር ህይወቴ ፡ በኤሜሬት ፕሮፌሴር ባህሩ ዘውዴ – ግለ ታሪክፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ የተከበሩ፡ የታሪክ ሊቅና እውቅ ምሁር ናቸው። ኢትዮጲያዊው የታሪክ ምሁር፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ በ1963፡ በከፍተኛ ማዕረግ ሲቀበሉ፡ ዶክትሬታቸውን ደግሞ በ1969 ከለንደን ዩኒቨርስቲ፡ የአፍሪካና የኦርዬንታል ጥናት፡ የትምህርት ክፍል አግኝተዋል።ትምህርታቸው በብዛት የሚያተኩረው በኢትዮጲያ ታሪክ፡ ዘመናዊው አለም፡ የብዙሀን መገናኛ ሚና፡ የምሁራን አስተዋጽኦ እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ ነው።በጣም ዝነኛ መጽሀፋቸው የዘመናዊ ኢትዮጲያ ታሪክን የተመለከተ ነው።
የታሪክ ጸሐፊ ትልቁ እሴቱ ለማንም የማያደላ(objective) መሆኑ ነው። የዘመናዊ ኢትዮጵያ ታሪክ የተሰኘው የባሕሩ ዘውዴ መፅሀፍ ከግለሰብ አስተያየት የነፃ በእውነታዎች የተሞላ ለሃቅ እንጂ ለሌላ የማያደላ በመሆኑ የአማርኛ የታሪክ ስነፅሁፍ ማስተርፒስ ነው። የባሕሩ ዘውዴ መፅሀፍት በነሲብ ሳይሆን በጥናት እና ምርምር የሚፃፉ ናቸው። ካሉን ጥቂት ሃቀኛ ምሁራን አንዱ ባህሩ ዘውዴ ናቸው!

Digital/Audio Book Files

    Br550.00

    The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.

    The book is available for borrowing. Select the number of days** the book can be borrowed. Standard borrowing duration is 7 days.
    Product total
    Options total
    Grand total
    -
    +

    ኤመሪተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ
    የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍልን በበላይነት መርተዋል፡፡በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ በተለያዩ ቦርዶች እና ማኅበራት ውስጥ በአባልነት፣ በአመራር እና በጥናት ሰፊ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ዘመናዊ ታሪክ በጥልቀት በመመርመር በርካታ ጥናታዊ ጽሑፎችን እና መጻሕፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡
    ፕሮፌሰር ባሕሩ ላበረከቷቸው ጽሑፎች ከዓለም አቀፍ ተቋማት እና ከሀገር ውስጥ የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝተዋል፡፡ በመምህርነት እና አመራርነት ያገለገሉበት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉን ሲያከብር “አርአያነት ያለው የላቀ አስተዋፅኦ” በሚል ሽልማት አበርክቶላቸዋል። በ2009 በማኅበራዊ ጥናት ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦም የበጎ ሰው ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
    የብሪቲሽ ካውንስል ስኮላርሺፕ፣ የብሪቲሽ አካዳሚ ፌሎሺፕ፣ ከፈረንሳይ መንግሥት የምርምር እርዳታ እና ከጃፓን ፋውንዴሽን ማኅበራት ጨምሮ ከተለያዩ አካላት በርካታ ሽልማቶችን እና ዕውቅናዎችን አግኝተዋል።
    ፕሮፌሰሩ ከሀገራችን እስከዓለምአቀፍ የበረከቱ መፅሐፍትን አንብበዋል። በአንድ ወቅት የትምህርት አቀባበል ሁኔታቸውን ያየው ሚስተር ታየር የተባለ የእንግሊዘኛ መምህራቸው እንዲህ ተንብዮ ነበር…”.አንድ ቀን ከመሬት ተነስቶ ባህሩ ወደፊት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሆን አትገረሙ” ብሎ ተናገረ።ደግነቱ እኔ ቁብ ስላልሰጠሁት የተለየ የፖለቲካ ፍላጎት አላሳደረብኝም።” ብለው ፅፈዋል።
    ለንባብ ያላቸው ፍቅር አስደናቂ እንደነበር የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ። እርሳቸውም እንዲህ ይላሉ። “ሳነብ ከመጠን በላይ የመመሰጥ ባህሪ(ዬ) አንዳንዴ ከልኩም ያልፍ ነበር።….እኔ ከንባብ ሰመመኔ ተነስቼ አብዬን “አየለን አሞት ነበር እንዴ?!” ብዬ ስጠይቃት በንዴት ” የታመምከውስ አንተ ፀበል የሚወስድህ አጥተህ ነው እንጂ” አለችኝ።” ይሉናል “ህብር ሕይወቴ” ግለ ታሪክ በተሰኘ መፅሐፋቸው።
    አሁን በጡረታ ላይ የሚገኙት አንጋፋው ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ፤ በfm addis 97.1 የ100 ቀናት “ለተሻለ ነገ እናንብብ” መርሃ ግብር ቢነበቡ ያሏቸውን ምርጥ 3 መፅሐፍት መርጠው ሰደውልናል።
    1- የሀዲስ አለማየሁ _ፍቅር እስከመቃብር
    2- የአምባሳደር ዘውዴ ረታ_ የኤርትራ ጉዳይ
    3- የበዓሉ ግርማ _ ኦሮማይ