ጥራት ላለው ህይወት!!!
ህይወት እንዳበበ አበባ ፈክታ፣ አምራና ተውባ፣ ደምቃ እንድትታይ ካሰፈለገ፥ በሰዎች መካከልም ስንመላለስ የግንኙነት መስመራችን የመከባበር ሀዲዱን ጠብቆ እንዲጓዝ ከሻትን፣ በስራና በንግዳችን በልዩነት መመረጥና መታወቅን ካሰብን፣ የፍቅርና የትዳር መንገዳችን የተደላደለና የተመቸ እንዲሆን ካስፈለገ፣ ኑሯችንን ማዘመንና ማቅለል ካለብን፣ አልባበሳችን የተስተካከለ፣ አነጋገራችን የታረመ መሆን ከተገባው፣ ከነበርንበት የተዘበራረቀ አኗኗር ተለየተን የተመጠነና ልከኛ ህይወት መምራት ከፈለግን ቁምነገሩ ያለው የንባብ ልምምዳችንን መፈተሹ ላይ ነው። በማንበብ ውስጥ ጥራዝነጠቅነት ይከስማል፣ አላዋቂነት ይጠፋል፣ አለሁ አለሁ ልታይ ልታይ ባይነት ይቀንሳል በምትኩም ትህትና በልባችን ይነግሳል፣ ሚዛናዊነት ይጎላል፣ ጨዋታችን ይደምቃል፣ ተሰሚነት ይጨምራል፣ ጥሩ አዳማጭ እንሆናለን፣ ቁጥብና የተረጋጋ ማንነት እንጎናጸፋለን ። እናም የንባብ ልምምዳችን ይዳብር።
ኢዮብ ጽጌ
Responses