እንደ ፍቅር ያለ አስተማማኝ ጥላ የለም
በፍቅር መኖር እረፍት ይሰጣል። ማጣትን ያስረሳል። ፍቅር ያለው ባለው ነገር ይረካል ፣ባለው ነገር ሌሎችን ያገለግላል፡፡ኑሮዬ ይበቃኛልን ያውቃል። በፍቅር የሚኖር የትላንት ማንነቱን አይረሳም፣ ዋጋ የከፈሉለትን ባለውለታዎቹን ያከብራል እውቅናም ይሰጣል። በፍቅር የሚሰራ፣ በፍቅር የሚኖር የተባረከበትን በረከት ያያል። በፍቅር የሚኖር በፍቅር የሚሰራ፣ በፍቅር የሚመላለስ ለሌሎች የሚጠቅም፣ ሌሎችን የሚያነሳ ሌሎችን የሚያሻግር ስጦታዎች በእርሱ እንዳለ ያምናል፥ በሌሎች ላይ ዋጋን ለመጨመር ፣ ሌሎችን ለማነፅ ፣ ሌሎችን ለመገንባት ፣ ሌሎችን ለማፅናናት እና ለማፅናት ተግቶ ይሰራል፡፡ እንደፍቅር አስተማማኝ የድካም ማረፊያ የሚያስጠልል ጥላ የለም። በፍቅር እንኑር፣ በፍቅር እንስራ!!!!!!
Responses