ማንበብ ወደ ስክነት የሚመራ የእረፍት መንገድ ነው።
ማንበብ ወደ ስክነት የሚመራ የእረፍት መንገድ ነው። ስታነብ የማወቅ ጉጉትህ ይጨምራል፣ የመጠየቅ ፍላጎትህ ይነሳሳል፣ የሰዎችን ሀሳብ ለመረዳት የሚያስችል የመከባበር አቅም ታጎለብታለህ፣ በማንበብ ውስጥ ራስህን ፈልገህ የማግኘት ጉጉትህ ከፍ ይላል፣ ከሌሎች ስህተት የመማር እድል ታገኛለህ፣ የተበላሸውን ለማስተካከል የሚያስችል ጥበብ ትቀስማለህ፣ ይህ የማስተዋልና የማመዛዘን አቅምህን ስለሚያዳብርልህ ክብርህ የማይደፈር፣ ስምህ የሚታፈር የተረጋጋ ማንነት ባለቤት ትሆናለህ። ይህንን ስብዕና ለመጎነፀፍ ዕለት ዕለት ጥቂት ጥቂት እናንብብ!!!!!!
Responses