ማንበብ ክፉ ሀሳባችንንማጥሪያ፣ ቆሻሻችንን ማጠቢያ ኤፆጵ ነው!

ሁልጊዜ በንባብ የሆነልኝን፣ ማንበብ የሰጠኝን ከፍታ፣ ያጎናፀፈኝን ነፃነት ለጉደኞቼ ፣ በየደረስኩበት በጨዋታ መሀል አነሳለሁ። አንድ ቀን ግን ለአንድ ወዳጄ ሳጫውተው ፣ በምን ጊዜህ ታነባለህ? ምን ብታነብ ነው እንዲህ በኩራት የሚያናግርህ ሲል ሁኔታዬ ያጫረበትን ጥያቄ ሰነዘረልኝ።

“የእውነት መለወጥ ከፈለክ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን ካለብህ፣ ሙያህን ማዘመን፣ ራስህን ማሰልጠን ከፈለክ፣ ሌሎች ያልሄዱበትን መንገድ መጓዝ ከሻትክ፥——አልኩት

“በቃ ከማንነትህ ክታብ ውስጥ ደብዛዛውን ገፅ ገልጠህ ማየት ከፈለክ፤ ውድቀትህን ሽንፈትህን ስንፍናህን ማየት ካለብህ……. ከወሬህ ጀርባ ያለውን ምክንያት የለሽ አሉባልታ ማስወገድ ከፈለክ ፤ ከቃልህ ጋር አብሮ ስለማይወጣው አፍነህ ስለምታስቀረው መጥፎ ሀሳብ፤ ሰብረህ ስለጣልከው ንፁህ ልብ፤ ስለ ውሸታምነትህ፤ ስለ ኩራትህ፤ በመጥፎ ቃላትህ  ህሊናቸውን ስላቆሰልክባቸው፤ ስለገፋሃቸው፤ ስለምትጠላቸው፤ ስላሴርክባቸው ስለጣልካቸው ፤እንቅፋት ስለሆንክባቸው ሰዎች  ያለማስረጃ እና ያለመረጃ ስላሳደድካቸው ወርቃማ ሀሳቦች ቆም ብለህ ማየትና ራስህን ከዚህ አይነት ልምምድ መነጠል ካለብህ፣ በስራህ መመስገን፣ በውሳኔህ መከበር ከፈለክ፣ የበደልካቸውን ለመካስ ከተነሳህ ” ብልጭልጭ ማንነትህን አውልቀህ ጠንካራው አንተነትህን ለማግኘት መጽሀፍትን መርምር፣እውቀትን ፈልጋት፣ ጥበብና ማስተዋልን ታድልሀለች። ያኔ ይኸው እንደኔ በኩራት የራስህን ከፍታ ትመሰክራለህ አልኩት። በአይኑም፣ በልቡም ፣ በሁለንተናውም አድምጦ ፣ ስጠኝ አንተ ለኔ ይሆናል የምትለውን ጠቁመኝ ብሎኝ፣ መልካሙን የህይወት ጣዕም አሸከምኩት። ማንበብ ክፉ ሀሳባችንንማጥሪያ፣ ቆሻሻችንን ማጠቢያ ኤፆጵ ነው።

ማንበብ ክፉ ሀሳባችንንማጥሪያ፣ ቆሻሻችንን ማጠቢያ ኤፆጵ ነው።

Related Articles

እንዲህ አነባለሁ!

እንዲህ አነባለሁ! • በራእዬ እና በምከታተለው ዓላማዬ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ! • የእኔን፣ የቤተሰቤን፣ የንግዴን፣ የመስሪያ ቤቴንና የሃገሬን ሁኔታ በሚያሻሽል ርእስ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ! • ያነበብኩትን…

Responses