የታንጉት ሚስጥር
A Book By - ብርሀኑ ዘሪሁን/Birhanu Zerihun
In Stock
የታንጉት ሚስጥር
Available Book Type
|
|
📗Printed
Book Info
Author - ብርሀኑ ዘሪሁን/Birhanu Zerihun
Category - ታሪካዊ ልብወለድ
Translated Book - No
Language - Amharic
Book Review
በታንጉት ምስጢር አፄ ቴዎድሮስ በተገቢው መንገድ ተገልፀዋል፣ ቁጭታቸው፣ ንዴታቸው፣ ኩሩነታቸው፣ መካሪነታቸው፣ ሀገር ወዳድነታቸው፣ ሀገረ የማቅናት ራዕያቸው፣ ለሠው ልጅ ያላቸው ክብር፣ የነጫጭባዎችን ከንቱ አላማ መረዳታቸው፣ የልቀ ጳጳስ አቡነ ሠላማ በኃይማኖት አባትነት ስም በኛው ሀገርና ደኃ ሕዝብ መቀለዳቸው ገብቷቸዋል ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ።
የቴዎድሮስ ራዕይ በዚያን ኋላ ቀር ዘመን ጎልቶ እንደ ወጣም ብርሃኑ ያስነብበናል። አመፀኞች፣ ተንኮለኞች፣ አሻጥረኞች የቴዎድሮስ አላማ እንዳይሳካ ምን ያህል ጥረት ያረጉ እንደነበር፣ አንዱን አሳካሁ ሲሉ ሌላው አየሾለከ እንዳወካቸው ፣ተሰፋ እንዳስቆረጣቸው በደንብ ያወሳል ደራሲው።
ስለ ዘር ልዩነትም የዚያን ግዜውን ዕውቀት ያስጨብጣል መጽሐፉ፣ በሕዝቡ መሐል ጨዋ ዘርና አይነኬ ዘር እንደነበረ፣ ታንጉት አፄው ያሳደጓት፣ ዝሪያዋ ቅማንት እንደነበረ በመግለፅ። ተወዳሹና ተከባሪው ዘር አማራ መሆኑን በማሳየትና ቅማንትና ወይጦ መሆን ምን ያህል እንደሚያሸማቅቅ፣ ታንጉትም ቅማንት በመሆኗ እየተሳቀቀችና አየተሸማቀቀች እንደምትኖር።
ገብሪዬ ደፋርና የውጊያን ስልት የሚያውቅ፣ የቴዎድሮስ ቀኝ ክንድ የነበረና፣ ታንጉትን የዳሩለት ማለፊያ ወታደር እንደነበረም ደራሲው ያወሳል። አክሊሉና ጋረድ ታላላቅ የዘመኑ ሠዎች በገብሪዬ ቅናት አድሮባቸው በመረባቸው ውስጥ በማስገባት ከቴዎድሮስ ጋር ለማጣላት እንደተመኙና እንዳልተሳካላቸው አብክሮ ይገልፃልም።
የቴዎድሮስ ዘመን መሪዎች ምን ያህል በምቀኞችና ሸረኞች እንደሚደናቀፉና አላማቸው እንዳይሳካ ብርቱ ጥረት መደረጉ በግዜውም የምናዬው መሆኑ አግራሞትን የሚጭር ነው።
ደራሲው ወደ ቀደመው ዘመን ወስዶን እውነታ እንድንረዳ ማድረጉ ምሥጋና እንዲቸረው የሚያደርግ ነው፣ መነበብ ያለበት ታላቅ ሥራ አንብቡ።



