ምንትዋብ
A Book By - ህይወት ተፈራ
In Stock
ምንትዋብ
Available Book Type
|
|
📗Printed
Book Info
Author - ህይወት ተፈራ
Category - ታሪካዊ ልብወለድ
Translated Book - No
Language - Amharic
Number of Pages - 227
Book Review
ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ስለ ምንትዋብ የተሰጠ አድናቆት፦
”ምንትዋብ” ከዚህ ቀደም ሕይወት ተፈራ ከጻፈቻቸው መጻሕፍት እጅጉን የተለየ ታሪካዊ ልቦለድ ነው። ይዛ የተነሳቻት ባለታሪክም፣ታሪኩ ያጠነጠነበት ዘመንም፣ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ድንግል ነው። ሳይነካ ቆይቷል።የሕይወት ብዕር ፣በእቴጌ ምንትዋብ አማካኝነት፣በፈጠራ ሥራወቻችን ውስጥ ችላ ተብሎ፣ወይም ተዘግቶ የነበረውን ዘመን ከፍቶና ገርስሶ፣ቋንቋን፣ውበትን፣ጥበብን፣ፍልስፍናን እና እንደ ፎክሎር ያሉ ዕንቁወቻችን አስቆጠረን።
እደግመዋለሁ፣የመካከለኛው ዘመን የታሪክ መጋረጃም በዚህ ልክ በሥነ-ጽሑፋችን ተገልጦ አያውቅም፣ንግስቶቻችንም በዚህ ልቦለድ ልክ፣እንደ ሰው በፍቅር ሲፈተኑ፣በጥበብ ረሀብ ሲናውዙ፣እንደ ሀገር መሪ ህያው ሐውልት ለማኖር ሲኳትኑ፣ሰላምን ለማዝነብ ሲባዝኑ ታይተው አያውቁም።
የቀደምት ሠዓሊዎቻችንን ሕይወት እና ፍልስፍና ምን ይመስል እንደነበረም በዚህ ልክ ፈትቶ ያቀረበልን ድርሰት ማግኘትም አስቸጋሪ ነው።
ደራሲዋ ትናንትናችንን ከዛሬያችን ጋር ያስተሳሰረችበት ክር ደግሞ ከምንም በላይ አበጀሽ የሚያሰኝ ነው!!! መልካም ንባብ።
Digital/Audio Book Files
Br480.00
The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.
ደራሲዋ ህይወት ተፈራ ከአሁን ቀደም ሁለት መጻሕፍትን ጽፋለች። ሁለቱም የተጻፉት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነበር። በእርግጥ ሁለቱም በተለያዩ ተርጓሚዎች ወደ አማርኛ ተመልሷል። የህይወት የመጀመሪያ መጽሐፍ Tower in the Sky በጌታነህ አንተነህ ማማ በሰማይ ላይ ተብሎ ሲተረጎም ሁለተኛው መጽሀፏ Mine to Win በህይወት ታደሰ ኅሠሣ ተብሎ በህይወት ታደሰ ተተርጉሟል።
ህይወት ሁለት አስደናቂ ባህሪያት ያላት ደራሲ ነች። Tower in the Sky ከገዟ ልምዷ ጨልፋ የጻፈችው memoir ነው። በባህሪው ኢልብወለድ ነው። የተጻፈው ግን ተነቦ በማይጠገብ ልብወለዳዊ የስነጽሁፍ ቅርጽ ነው። የተቀሩት ሁለቱ የህይወት መጻሕፍት ግን ታሪካዊ ልብወለዶች ናቸው። ህይወት በልብወለድም በኢልብወለድም እኩል ትራቀቃለች። ሌላው የደራሲ ህይወት አስደናቂ ችሎታ በአማርኛም በእንግሊዝኛም እኩል ሃሳቧን የመግለጽ ብቃቷ ነው።



