ሰው፣ ግብረገብና ሥነ ምግባር የዘመናችን ቁልፍ ጉዳዮች
A Book By - ጠና ደዎ / Tena Dewo

In Stock
ሰው፣ ግብረገብና ሥነ ምግባር የዘመናችን ቁልፍ ጉዳዮች
Available Book Type
|
|
📗Printed
Book Info
Author - ጠና ደዎ / Tena Dewo
Category - Non-Fiction
Publisher - AAU Press
Translated Book - No
Language - Amharic
Number of Pages - 502
Book Review
ይህ መጽሐፍ በተለይ ለአማርኛ ቋንቋ አንባብያን የግብረገብና ሥነ-ምግባር ፍልስፍናን የሚያስተዋውቅ ነው።
… ጸሐፊው ባነሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በቂ ምሁራዊ ይዘት ያላቸውን ግብኣት ለማካተት ችለዋል። እንዲሁም ስለግብረገብ ፍልስፍና ያላቸው ዕውቀትና ይኼንንም ከዕለት ተዕለት ችግሮቻችን ጋር አሰናስለው ለማየት ያደረጉት ሙከራ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ነው። ይኸም መጽሐፉን የማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከሞራል ፍልስፍና አንጻር ለመቃኘት የሚያስችል ስለሚያደርገው ለጠቅላላ አንባቢው ጠቀሜታ እንዲኖረው አድርጎታል።
በቀለ ጉተማ (ዶር)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና ትምህርት ክፍል
በሥነ-ምግባር ዙሪያ የተጻፉ ብዙ መጻሕፍት የሉም። ከዚህ አንፃር ይህ መጽሐፍ ዋጋው ላቅ ያለ ነው። መጽሐፉ ለሥነ-ልቦና አማካሪዎች፣ ለማኅበራዊ አደራጆችና ለሕብረተሰብ ግንኙነት ተመራማሪዎችም እንደጠቅላላ ንባብ እና ለተጨማሪ የምርምር ሐሳብ ማነሳሻ ይጠቅማል። በዚህ መልኩ መጽሐፉ በመስኩ ለሚፈለግ ጠቅላላ ዕውቅት ግንባታ ከሚኖረው አስተዋፅኦ በተጨማሪም የተጻፈበት ቋንቋ ሀገርኛ በመሆኑ፣ ተደራሽነቱ የሰፋ ይሆናል።
ያዕቆብ አርሶና (ዶ/ር)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ከፍል
Digital/Audio Book Files
Br144.00