ምንዱባን

In Stock

ምንዱባን

Available Book Type

|

|

📗Printed

Book Info

Category -

Translated Book - No

Language - Amharic

Book Review

ዝግን ቁምነገሮች ከ”ምንዱባን” መፅሐፍ (Le Mesi’rebles)
(እ.ብ.ይ.)
ቪክተር ሁጎ (Victor Hugo) በ19ኛው ክፍለዘመን የኖረ ፈረንሳዊ ደራሲና ገጣሚ የነበረ ሠው ነው፡፡ ሁጎ ከሐገሩ ፈረንሣይ ውጪ የታወቀበት ስራው በአማርኛ ምንዱባን ወይም መከረኞቹ ተብሎ በሁለት በተለያዩ ተርጓሚዎች የተተረጎመው Le Mesi’rebles የተባለው መፅሐፉ ነው፡፡ ከLe Mesi’rebles በፊት በ1831 ያሳተመው መፅሐፍ The Hunchback of Notre-Dame (French: Notre-Dame de Paris) ይባላል፡፡ እርግጥ ነው ሁጎ መጀመሪያ የታወቀው በሁለት የግጥሞቹ ስብስብ መፅሐፍ ነበር፡፡ (Hugo is known primarily for his poetry collections, such as Les Contemplations (The Contemplations) and La Légende des siècles (The Legend of the Ages)
Le Mesi’rebles የተባለውን መፅሐፍ ዮሐንስ ገ/ፃዲቅ የተባለ ተርጓሚ *ምንዱባን* በሚል ስያሜ ወደአማርኛ መልሶልናል፡፡ ተርጓሚው ምንዱባን ማለት የምድር ጎስቋሎች ማለት ነው ሲል በመፅሐፉ ይነግረናል፡፡ ተርጓሚውን እያመሠገንን ዛሬ ከዚህ መፅሐፍ አንዳንድ ሃሳቦችን ዘግነን ከሃሳባችን ጋር እናስተያያለን፡፡ አስተያይተንም አዲስ ሃሳብ እንሰራበታለን፡፡
በመፅሐፉ የተቀመጠ አንድ ሃሳብ እናገኛለን፡፡ ሃሳቡ እንዲህ ይላል፡-
‹‹ማንም ሠው ቢሆን የባሕርን ውሃ ወደዳር እንዳይወጣ ለማገድ እንደማይቻለው ሁሉ አዕምሮም ውስጥ ሃሣብ እንዳይገባ መከልከል አይችልም፡፡››
እውነት ነው! አዕምሮ የሃሳብ ማረፊያ ቤት ነው፡፡ ሃሳብ እንዳሻው ዞሮ ዞሮ የሚገባውና የሚወጣው አዕምሮ ውስጥ ነው፡፡ ክፉም ይሁን ደግ ሃሳብ አዕምሮ ውስጥ እንዳይገባ ዘበኛ ቀጥሮ መከልከል አይቻልም፡፡ ባይሆን የሚገባውን ሃሳብ መግዛትና መቆጣጠር ነው የሚቻለው፡፡ የገባው ሃሳብ እኛነታችንን እንዳይቆጣጠር በመልካም አስተዳደር ልንገዛው ይገባል፡፡ በመልካም አስተዳደር ያልተዳደረ ሃሳብ እንዳሻው ይዞን ይከንፋል፡፡ ስለዚህ መቆሚያ ታኮ ያለው ሃሳብ ማበጀት ይጠቅማል፡፡
በሌላው በመፅሐፉ ገፅ ስለእውነት እንዲህ ይለናል፡-
‹‹እንቁ ጨለማ ከወረሠውና ጥልቀት ካለው መሬት ውስጥ ተፈልፍሎ እንደሚገኝ ሁሉ እውነትም ከማሠብና ከማሠላሠል ብዛት ይደረስበታል፡፡››
እርግጥ ነው ይሄ ሃሳብ እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ እውነት ላይ በማሠብ ብዛትና በማብሠልሠል ከፍተኛ አቅም መድረስ ከባድ ቢሆንም ብርቱ ሆኖ አሰላስሎ ለጠየቀ ግን በመጨረሻ ይሆንለታል ብዬ አስባለሁ፡፡ የሠው ልጅ በሃሳቡ ዓለሙን የሚመረምር ከሆነና ተፈጥሮን እንዳሻው እየጠየቀ ካሠላሠለ አንዳች እውነት ይገለጥለታል፡፡ ያሠበ ሁሉ ይሄን ያደርጋል ማለት ግን አይቻልም፡፡ የምናስብበት መንገድና አስተሳሰባችንን እየሞረድንና እየጠረብን እንዲሁም እያሻሻልም መሄድ ከቻልን ግን እውነት ጋር ለመድረሳችን መላልሠን ማሠባችን ዋስትና ይሆነናል፡፡
ወዳጆች ሕሊናችን በተፈጥሮ የተሠጠን ፀጋችን ቢሆንም በአግባቡ እንዲሠራ፣ ሠላሙንና ዓላማው የተጠበቀ እንዲሆን እህል ውሃ የምንሠጠው ግን እኛው ራሳችን ነን፡፡ መፅሐፉም እንዲህ ሲል ስለደካማ ሕሊና ይናገራል፡-
‹‹ደካማ ሕሊና ምንጊዜም ነገሮችን የሚመለከተው ዓይኖቹን በጥቁር ጨርቅ ሸፍኖ ነው፡፡ መንፈሳችን የራሱን አድማሳት በማጥበብም ይሁን በማስፋት ይሠራቸዋል›› …. ይለናል፡፡
እውነት ነው! ‹‹ቅን ሠዎችን ቅንነታቸው ትመራቸዋለች፤ ጠማማዎችን ጠማማነታቸው ትጥላቸዋለች›› እንዲል ቅዱስ መፅሐፍ ጠንካራ ህሊናን ለመፍጠር መጀመሪያ ለራስ ቅን መሆን ያስፈልጋል፡፡ ቅን አስተሳሰብ የመንፈሳችንን አድማስ አስፍቶ ሩቅ እንድናስብና በራሳችን ትንሽ አጥር ታጥረን እንዳንጠብብ ይረዳናል፡፡ የምናይበት አተያይ ለሕይወታችን ትርጉም ወሳኝ ነውና አስፍተን እናስብ፡፡
በመጨረሻም መፅሐፉ ስለፍቅር ያነሳውን ሃሳብ ላንሳና ልሠናበት፡-
‹‹ድንጋይ ከሆንክ ትልቅ ድንጋይ ሁን! ዛፍና የቅጠላ ቅጠል ዘር ከሆንክ ፍሬ፣ ሠው ከሆንክ ደግሞ ፍቅር ይኑርህ፡፡›› ….. ይልና
‹‹አንጎል በፍቅር ከተሞላ ተልካሻ ሃሣብ ከጭንቅላት ውስጥ መግባቱን ያቆማል››…. ይለናል፡፡
እርግጥ ነው ፍቅር የበጎ ነገሮች መክፈቻ ሲሆን በዛው ልክ የክፉ ነገሮች መዝጊያም ነው፡፡ በፍቅር ያልተዘጋ ሴራ የለም፡፡ በፍቅር ያላበቃለት ጦርነት የለም፡፡ በፍቅር አደብ ያልገዛ ጦረኛ የለም፡፡ ፍቅር የነገሮች መጠቅለያ፣ የበጎ ነገሮች መሠረት ነው፡፡ የሠው ልጅ ጭንቅላቱን በፍቅር ከሞላ ክፉ ሃሳቦችና ተልካሻ ሴራዎች ወደእሱ ድርሽ አይሉም፡፡ በፍቅር የተሞላ ጭንቅላት ትርፉ በፍቅር መኖር ነው፡፡
ወዳጆች ሠው*ነታችን በፍቅር ካልተሞላ አውሬነታችን ብቅ ይላል፡፡ እንደሠው የተሠጠን ክቡርና ድንቅ የሆነው አዕምሯችን የደመነፍስ ስሜትን ማስፈፀሚያ ተራ ዕቃ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሠውነታችንን በፍቅር ሞልተን፣ ደመነፍሳችንን ገዝተን ድንቅ ሃሳቦችን እናምርት የዕለቱ መልዕክት ነው፡፡
መጽሐፉን ታነቡ ዘንድ ግብዣዬ ነው፡፡ ያነበባችሁትም ሃሳባችሁን ታካፍሉን ዘንድ ትጉ፡፡ ሐሳብ አስተያየታችሁ ያስፈልጋልና ወዲህ በሉ፡፡
ቸር ጊዜ!
_____________________________
እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
ረቡዕ ሠኔ ፳ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.

Digital/Audio Book Files

    Br280.00

    The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.

    The book is available for borrowing. Select the number of days** the book can be borrowed. Standard borrowing duration is 7 days.
    Product total
    Options total
    Grand total
    -
    +