ፍቅር እስከ መቃብር
A Book By - ሀዲስ አለማየሁ
In Stock
ፍቅር እስከ መቃብር
Available Book Type
|
|
📗Printed
Book Info
Author - ሀዲስ አለማየሁ
Category - Fiction
Publisher - ማንኩሳ
Translated Book - No
Language - Amharic
Number of Pages - 552
Book Review
በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የቀረበ ልብ ወለድ ሲሆን ሰብለ ወንጌል እና በዛብህ የሚባሉ የሁለት ገፀ ባህሪያን ፍቅር ላይ ያተርኩራል። ሀዲስ ዓለማየሁ “ፍቅር እስከ መቃብር” በተሰኘው የአማርኛ ረዥም ልቦለድ ሥራቸው “ለኢትዮዽያ ሥነጽሁፍ አዲስ ምእራፍ ከፋች” የሚል ሞገስ ያገኙ ሲሆን፣ በዚሁ ኪናዊ ሥራቸውም ፋሽስት ኢጣሊያ ከወጣ በኋላ ብዚዎቹ ኢትዮዽያውያን ደራስያን ያላተኮሩበትን የፊውዳል ኢትዮዽያን ገፅታ በተለየ ትኩረት በስፋትና በጥልቀት በመዳሰስ ኪናዊ በሆነ የቋንቋ ኃይልና ውበት የገለጹ፣ በፊውዳሉ ሥርዓት ላይ ያመፁ እንደ ጉዱ ካሣ፣ በዛብህ፣ ሰብለወንጌል፣ አበጀን የመሳሰሉ ሕይዋን ገፀ ባሕርያት በመሳል- በለውጥ የትግል መንፈስ ላይ ለነበረው አዲስ ትውልድ ሀዲስ ራዕያቸውን በጥበብ አጋርተዋል። በአጻጻፍ ብልሃቱ በአማርኛ ሥነ ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ አዲስ ፈር በቀደደው የ”ፍቅር እስከ መቃብር” ድርሰታቸው በሁለት የውጭ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። ደራሲ ሐዲስ አለማየሁ የኖሩበትን የፊውዳሉን ዘመን ባህል፣ አስተሳሰብ እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ በዘመኑ ያልተፈጠረን አንባቢን ጭምር በምናቡ ዘመኑን እየሳለ ያልኖረበትን ዘመን ጣእም እንዲያጣጥም ያስቻለበት ድንቅ የፍቅር መጽሐፍ ነው። በኢትዮጵያ ዘመናዊ የአማርኛ የልቦለድ ስነጽሑፍ ታሪክ በብዙ ጸሐፍት ቁንጮ ስፍራን የያዘም ነው።
Digital/Audio Book Files
Br500.00




