ምን ሆኛለሁ / Min hognalehu
A Book By - ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ቴዎድሮስ ተክለ አረጋይ Tigist Waltenigus and Tewodros T/ Aregay

In Stock
ምን ሆኛለሁ / Min hognalehu
Available Book Type
|
|
📗Printed
Book Info
Author - ትዕግስት ዋልተንጉስ እና ቴዎድሮስ ተክለ አረጋይ Tigist Waltenigus and Tewodros T/ Aregay
Category - ስነልቦናዊ psychological
Publisher - ማንኩሳ Mankusa
Translated Book - No
Language - Amharic
Number of Pages - 240
Book Review
“የምታደርጉት ድርጊት ግራ አጋብቷችሁ ‘ምን ሆኛለሁ?’ ብላችሁ ከጠየቃችሁ ይሄ መፅሀፍ ልጅነታችሁን በመመርመር ራሳችሁን በተሻለ እንድትረዱ ያግዛችኋል”።
በተጨማሪም “በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ወይም በቲቪ የምታውቋቸው ነጋዴዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች የሚያደርጉት ድርጊት አልገባ ብሏችሁ ‘ምን ሆኖ ነው?’ ወይም ‘ምን ሆና ነው?’ የሚል ጥያቄ ከፈጠረባችሁ ይሄ መፅሀፍ ጥሩ የፅንሰ ሀሳብ መነፅር ይሰጣችኋል ”
Digital/Audio Book Files
Br500.00
The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.
 የወራት ድካም ነው ። እኔን በግል ለቀናት ካልተገደድኩ ከቤት እንዳልወጣ ያደረገኝና ብዙ ማህበራዊ ግንኙነቴን ያቋረጠብኝ ስራ ነው ። ድካማችን ለመልካም በመሆኑ ሁለታችንም ደስተኞች ነን ። አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ ፣ ከማለፉ በፊት ከሚሰራቸው ስራዎች መሀል አንዱ ( ለትዕግሥት ዋልተንጉሥ እና ለእኔ  ) ይህ ” ምን ሆኛለሁ ? ” ብለን የሰየምነው መጽሐፍ ነው ። ” ምን ሆኛለሁ ? ” ለትዕግሥት ዋልተንጉሥ የመጀመሪያዋ ፣ ለእኔ ደግሞ 7ኛ ስራችን ነው ። የሁለታችን ጥምረት ትልቅ ስራ የፈጠረ ይመስለኛል ።
        የስነልቦና ባለሙያዋ ትዕግሥት ዋልተንጉሥ ከ15 ዓመት በላይ በምክክር አገልግሎት ላይ ሰርታለች ። በ” እርቅ ማዕድ ” የሬዲዮ ፕሮግራም እንዲሁም በEBS ቴሌቪዥን ” እንመካከር ” ፕሮግራምን አዘጋጅታለች ። እኔ መጠየቅ ፣ ሀሳቦችን የተቻለኝን ያህል ውስጥ ድረስ ገብቼ ለመረዳት መሞከር ፣ ቀላል እና ልብ ደረስ አማርኛን መጻፍ እችላለሁ ። ሁለታችን ” ምን ሆኛለሁ ? ” ን ከማንም ቀድመን ራሳችን ወደነዋል ። እኔ በግሌ እስካሁን በጽሑፍ ከሰራኋቸው መጻሕፍትም ፣ ድራማዎችም ሁሉ የእኔ ለምለው ሕዝብ የማበረክተው ትልቁ ስራ ይህ በቅርቡ የሚወጣው መጽሐፍ እንደሚሆን አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ ። በቀላሉ የምማልል እና በራሴ ስራ የምመሰጥ ሰው አይደለሁም ። ” ምን ሆኛለሁ ? ” ግን እንደዚያ አይነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጎኛል ። ይሄ ስሜት ነገ እናንተ ላይ እንደሚጋባ አምናለሁ ።
        ” ምን ሆኛለሁ ? ” ን በመስራቱ ሂደት ለእኔ ትልቁ የስነልቦና ት/ቤት የገባሁ ያህል ተሰምቶኛል ። የራሴን ፣ የቤተሰቤን ፣ የወዳጆቼን ፣ በቅርብም በርቀትም የማያቸውን ኢትዮጵያውያን ፣ ዝነኛ ሰዎችን ፣ ፖለቲከኞችን ፣ የእውቀት ሰዎችን ለየት ያሉ ባህርያት ለመረዳት ፣ ምክንያታቸውን ለመገመት ፣ ሰውን በሚመለከት ፈራጅ ላለመሆን ፣ ሰው ማለት አሁን አብሮን የሚኖረው ወይም የሚሰራው ብቻ ሳይሆን የእስከዛሬውን – ይበልጡንም ልጅነቱንና አስተዳደጉን እንደሆነ እንድገነዘብ ረድቶኛል ።
       ” ይህን መጽሐፍ የሚያነቡ ሰዎች ራሳቸውንና የሚያውቋቸውን ሁሉ እንዲፈትሹ ፣ እንዲረዱና እንዲያግዙ እጅጉን ይረዳቸዋል ። ፖሊሲ አውጪዎች ለፖሊሲ ጥናት ይጠቅማቸዋል ብዬ አምናለሁ ። ” ይህን ያለው አንድ የአዕምሮ ሀኪም ነው ። ይህን  አስተያየቱን በመጽሐፉ ላይ ታገኙታላችሁ ። ዛሬ ላይ ከሚታይ የሰው ባህሪ ተነስተን ” እገሌ ማለት እንዲህ ነው ። ይህን ያደረገው ሆን ብሎ እኛን /እገሌን ለመጉዳት ነው ” እንላለን ። ከሂደቱ ይልቅ የመጨረሻ ውጤቱ ያሳስበናል ። ማንም ከባዶ ሜዳ ተነስቶ ምንም እንደማያደርግ ነው የስነልቦና ሰዎች የሚያምኑት ።
        በተለይ አሁን ባለንበት ጊዜ ” ምን ሆኛለሁ ? ” መጽሐፍ እጅጉን ያስፈልጋል ። መንግሥት ወይም ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በሚሊዮን ቅጂ አባዝተው በየቤቱ ቢያዳርሱና ልክ አሽከርካሪዎች የአሽከርካሪ ቀበቶ ተገደው አስረው ለሕይወታቸው ጠቃሚ እንደሆነው ከዚያ በላይ ፋይዳ ያለው ስራ እንደሆነ አምንበታለሁ ። አሁን ጉዳዩ የራስን ስራ ማስተዋወቅ ፣ ብዙ ቅጂ መሸጥና ከዚያ ገንዘብ ማግኘት አይደለም ዋናው ዓላማ ። እርግጥ ነው ብዙ ሲሸጥ በዚያው ልክ የገንዘብ ጥቅሙም አለ ። ይሁንና ግን ሰዎች መጽሐፉን ከገዛ ወዳጃቸው ተውሰው አንብበው ” በቀጣይም ቤቴ ሊኖር የሚገባ መጽሐፍ ነው ” ብለው ሲያምኑ ቢገዙ እሱም ይስማማናል ። ብቻ ” ምን ሆኛለሁ ? ” ከማንም ቤት ባይጠፋ ምኞታችን ነው ።
 
		



