ማሙሽ
A Book By - ሚካኤል አዝመራው Michael Azmeraw

In Stock
ማሙሽ
Available Book Type
|
|
📗Printed
Book Info
Author - ሚካኤል አዝመራው Michael Azmeraw
Category - Fiction
Translated Book - No
Language - Amharic
Number of Pages - 208
Book Review
ደራሲው በገፀ-ባህሪያቱ በኩል የሰው ልጅን አንድነትና ሶስትነት ያሳየናል። ቆይ! ድንጋዩን ቁጭ አድርጉና ተከተሉኝ ፤ እንድንግባባ።
በመጀመሪያ በዚህ መጽሐፍ የተነሳው ትልቁ ሀሳብ የሰው ልጅ አንድ የሚኖርለትም፤ የሚያኖረውም ሱስ(ዕፅ) አለውም ያስፈልገዋልም የሚለው ነው። ሱሱ መጥፎም ይምሰል ጥሩ ፤ ከፍ ያለም ይምሰል ዝቅ በእያንዳንዳችን ህይወት ውስጥ መኖሩ አይቀሬ ነው።
በእኔ አረዳድ የዓለምን ትርጉም የለሽነት የሚያስረሳን(የሚያዘናጋን) ሱስ ያስፈልገናልም አለንም። የትኛውም ዓለማዊ ሩጫ ከዚህ ዕፅ ይመደባል።ከየትኛውም ወጥቶ መግባት፤ መገፋፋት፣ መሯሯጥ፣መራወጥ ወዘተ ጀርባ ያለው ይህ ዕፅ ነው። አብዛኛው የሰው ልጅ በዚህ ተራ በሚመስል የህይወት ምልልስ የተጠመደ ነው። ከአንዱ መሰናክል ወደ አንዱ፤ ከአንዱ ምኞት ወደ ሌላው፤ከአንዱ አላማ ወደ ሌላ አላማ እየተሸጋገረ እስትንፋሱ ህቅታ ድረስ ይኖራል።
ገፅ 71 ላይ እንዲህ ይላል:-
“እነዚህ ከእንቅልፋቸው ለምን እንደሚነቁ ያውቃሉ፤ ያዙትም አልያዙትም የሆነ የሚያሯሩጡት ነገር አላቸው። እኔ ግን ህይወት ‘ላንተ የሚሆን ድራማ የለኝም ዝም ብለህ የሌሎቹን ኑሮ መመልከት ትችላለህ’ ብላ ያገለለችኝ መስሎ ይሰማኛል” ይላል።
ልክ ነው፤ ህይወት በየጊዜው የተለያዩ ድራማዎችን እየፈጠረች ትርጉም የለሽነቷን ለማስረሳት ዘወትር ትታትራለች። የሰው ልጅም ይህንን ውጣ ውረድ የሚጠላው ይምሰል እንጂ፤ የምሬት ቃላትም ከአፉ ይውጡ እንጂ ነገርየውን ይፈልገዋልም፤ ያስፈልገዋልም።
“ከሸክም ሁሉ ሸክም የሚሸከሙት አለመኖር ነው። “እንዲል ፈላስፋው ባዶነትን መሸከም የምንችልበት ጫንቃ አብዛኞቻችን ጋር የለም።
ገፅ 169 ላይ እንዲህ ይላል:-
“በየጊዜው ራሱን እየሸወደ የሚኖርበት አንድ ተጨማሪ ውሸት እስካገኘ ድረስ ሌላ ነገር አይፈልግም”
የአብዛኞቻችን ኑሮ ይህንን ይመስላል፤ ነገር ግን ከውሸት ዓለም መንቃቱም ደግሞ የራሱ የሆነ ከባድ ሸክም አለው። በመጽሐፉ ገፅ 70 ላይ
“ከነቃሁ መጋፈጥ የማልችላቸው እውነቶች ያሳድዱኛል” እንዲል ካለንበት የውሸት ዕፅ ተላቀን ወደ እውነት መንቃት የሚያስከትለውን ማለቂያ የለሽ የጥያቄ ውርጅብኝ ያለ መልስ ለመሸከም የሚያስችል ጫንቃ እስክናበጅ ድረስ ውሸታችንን እያደስን መኖር ተመራጭ ይመስለኛል።
Digital/Audio Book Files
Br300.00
The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.
ከመሰጡኝ አረፍተ ነገርና ሀረጎች መካከል ጥቂቱን:-
“በጊዜ ራስህን አለመግደል አንዱ ክፋቱ ይሄ ነው ። ዓይንህ እያየ የምትፅየፈውን ሰው ትሆናለህ “
“ከመሸነፍ በላይ ጎትጎተው ያስጀመሩትን ጦርነት መሸነፍ የከፋ ነው”
“የምተኛበት አልጋ እንጂ የማየው ህልም የለኝም”
“ምንም እውነት አንተ ጋር ብትሆን እንባህ ሲበዛ ግን ለመታመን እየጣርክ ይመስላል”
“አሸናፊ እንደመሆን ምን ትዕግስተኛ የሚያደርግ ነገር አለ”
“የሚያስገርማትን ማወቅ የበለጠ እሷን እንዲያውቅ አደረገው”
“እንደው ሲመቻቸው ጎረበጣቸው”
“በተኩላ ለምድ የሚደበቅ በግ እንዴት አያሳዝን”
“ሌሎች በፍቅር ስም ሲጠሉኝ እሱ በጥላቻ ስም ወደደኝ”
“ዙሮ ተዟዝሮ የሚችሉትን አድርገው የቀረውን ደግሞ “የጀንበር አመል ነው” እያሉ ማለፍ ነው እንጂ በነጋ ቁጥር ለሌለው መሸበት ተብሎ እየታዘነማ እንዴት ተብሎ ይዘለቃል”
“ከፈጠርኩት በኋላ መልሶ የሚፈጥረኝን ነገር እፈጥራለሁ”
“ታሪክ ራሱን አይደግምም፤ እኛ ነን ስህተታችንን የምንደግመው”
“ጥሩ የውሸት ታሪክ እንድነግራችሁ ከፈለጋችሁ ትንሽ እውነት ስጡኝ”
“ወሲብ ወሲብ ትልና መልሰህ አምላክ አምላክ ትላለህ። የሆነ ወንጌላዊ ለመሆን ተፈጥሮ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር የጠለፈው ዲያቆን ነው የምትመስለኝ “
“ተራ ህይወት በሌለበት ተአምር ምን ይሰራልኛል?”
“እዚህ ዓለም ላይ ሊቆጣጠርህ ነው እንጂ ሊወድህ የሚፈልግ የለም። አንተም ከኩራትህ ፍርሃትህ ስለሚበልጥ ትንበረከክላቸዋለህ”
********