ንባብ በአዲስ ሀሳብ ለመመራት!!!
የሰው ልጅ ምክንያታዊ፤ የሚጠይቅና የሚመራመር መሆኑየታመነ ነው፡፡ በዚህ አስተሳሰብ መሰረትም ህዝባችን ለሚገጥሙት ችግሮች ዘመኑን የዋጀ፣በዕውቀት ጎዳና የሚራመድ በማስተዋልና በሥርዓት የሚጓዝ ትውልድ ማፍራት ይኖርበታል። ይህን ማግኘት የሚቻለው ደሞ ለንባብ ምቹ ሁኔታ በመዘርጋት ሲሆን ለሁላችንም የምመኘው ነገር የሁላችንም ዛሬና ወደፊታችን በንባብ የምንበረታበት፣ መፅሐፍቶችን የምናገላብጥበትና በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከራሳችን ሃሳብ ጋር እያዋደድንን እየዋጀን በአዲስ ሃሳብ የምንሠራበት፣ራሳችንን የምናዘምንበትና የምንለውጥበት፣ እንዲሁም ድህነትን የምናሸንፍበት፣ ይሆን ዘንድ ከበፊቱ የበለጠ የንባብ ባህላችን እንዲዳብር በመናፈቅ ነው።
Responses