ማንበብ እንደ አዲስ ሰርቶኛል

የስራ ባልደረባዬ ናት ሁሌ እጄ ላይ መጽሀፍ ታያለች፣ በወሬዬ መሀልም እንትና ምን ብሏል መሰለህ የሚል የደራሲያን ስምና ሀሳብ ስሰነዝር  ታዝባኛለች። አንድ ቀን –

የምታነበውን ሁሉ ግን እውን ትኖረዋለህ?” ስትል ጠየቀችኝ፥

ይህ የብዙ ሰው ጥያቄ ይመስለኛል፥- የማነበውን ሁሉ ለመኖር የምችልበት ልዕልና ላይ አልደረስኩም ግን እየጣርኩ ነው በማንበቤ ያገኘሁትን የአስተሳሰብ አድማስ ምጥቀት፣ የሰዎችን ስሜት መረዳት እኔ አውቀዋለሁ። ማንበብ እንደ አዲስ ሰርቶኛል ግልፍተኝነቴን የታዘብኩበት፣ የተረጋጋና ጭምት የሆንኩበት፣አላስወራ የሚል ችኩልነቴን የገታሁበት ፣ ጥሩ አዳማጭነትን ያገኘሁበት ስለሆነ ማንበቤን እቀጥላለሁ” ስል መለስኩላት። የሰጠሗት መልስ ያስደሰታት ይመስለኛል።ማንበብን ሳስበው ይደክመኛል፣ እንዴት እንደምለምደው አላውቅም፣ እፈልጋለሁ ግን አልቻልኩም ብላ በርታ በሚል ግማሽ ዕይታ ጨርፋኝ አልፋ ሄደች።

Related Articles

ለዚህ ነው ማንበብ የሚያስደስተኝ፣ አንባቢ ሰው የሚያስቅቀናኝ፣ መጽሀፍት የሚያጓጉኝ!!!

አንባቢ ሰው አንባቢ ሲናገር አይደነቃቀፍም፤ ሃሳብ አይነጥፍበትም። እንዲያውም ቃላት ለሃሳቦቹ ይሰግዳሉ። ቋንቋ ይታዘዘዋል። የቃላት ሃብቱ ንግግሩ በጉጉት እንዲደመጥ ይጎተጉታሉ። አንባቢ ሰው ትልቅ የሃሳብ ጎተራ አለው።…

Responses