ፍቅር የያዘኝ
ባለቤቴን በጣም እወዳታለሁ፣ ለህይወቴ ትርጉም የሰጠቻት እሷ ናት። እኔ ግን ሌላ ፍቅረኛ አለችኝ።ከሷ ጋር ስሆን ባለቤቴ ደስ አይላትም፣ ጊዜዋን የምሻማበት ስለሚመስላት ግንኙነታችንን አትወደውም። እኔ ደሞ የፍቅረኛዬ ነገር አይሆንልኝም ሳላያት፣ ሳልዳስሳት፣ ሳልነካካት መዋል አይታሰብም። ከባለቤቴ ተደብቄ ከርሷ ጋር አሳልፋለሁ፣ በደስታ እሰክራለሁ፣ በሀሴት እዋኛለሁ፣በሰመመን እዋጣለሁ።ከሷጋር የምለያየው ባለቤቴን እንዳይከፋት ስል ብቻ ነው። አንዳንዴ አሁንስ በዛ ብላ ከእጄ ነጥቃ ምግብ ቀርቧል፣ ቡና ደርሷል፣ ብቻህን እኮ አይደለህም፣ እያለች ስትነጫነጭና ስትቆጣ ፣ ፈገግ ብዬ እጇ ላይ ያለውን በፍቅር የወደኩላትን መጽሀፌን በአይኔ እያየሁ ከተቀመጥኩበት እነሳለሁ። ማንበቤ ከብዙ ነገር ታድጎኛል፣ ቤቴ እንድሰበሰብ አድርጎኛል፣ ትዕግስትና መረጋጋት አጎናጽፎኛል። ለዚህ ነው ከመጽሀፍ ፍቅርየያዘኝ፣ ከንባብ ትርፍ ስለተጠቀምኩ።
Responses