ህይወት በማንበብ ትዋባለች፣ ታብባለች፣ ትፈካለች።
ህይወት የምትሸነፈው በትምህርት ብዛት ወይም ረቂቅ እውቀቶችን በመረዳትብቻ አይደለም። ኑሮን የተሻለ ለማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ እራስን የተሻለ አድርጎ መገኘት ነው። በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በስነልቦና፣ የአላማ ሰው በመሆን የተሻለ ሆኖ መገኘት።ለዚህ ደሞ ቁልፉ ማንበብ ነው። ህይወት በማንበብ ትዋባለች፣ ታብባለች፣ ትፈካለች። ሕይወት ውብ እንድትሆን፣በመለወጥ መንገድ እንድትጓዝ ምርጫችሁን አስተካክሉ።
የምትውሉበትን አካባቢ ስትለውጡ ፣ የምታዩትን ማሕበራዊ ሚዲያ ስትለውጡ ፣ የምትይዙትን የቅርብ ጓደኛ ስትለውጡ ፣ የምታነቡትን መጽሐፍ ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡በየቀኑ በመደጋገም የምታደርጓቸውን ልማዶች ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡
ራሳችሁ የማይሆን ምርጫ እየመረጣችሁ የማይሆን ሕይወት ውስጥ ስትገቡ ብትነጫነጩ ምንም አታመጡም፡፡ስለዚህ የለውጡ መንገድ የማንበብ ምርጫ መፍቀድ ነው። መጽሀፍትን መወዳጀት ነው። ከእናንተ የህይወት አላማ ጋር የሚሄዱትን መርጣችሁ አንብቡ፣ ተለወጡ። የዕለቱ መልዕክታችን ነው።
Responses