ፍቅር የያዘኝ

ባለቤቴን በጣም እወዳታለሁ፣ ለህይወቴ ትርጉም የሰጠቻት እሷ ናት። እኔ ግን ሌላ ፍቅረኛ አለችኝ።ከሷ ጋር ስሆን ባለቤቴ ደስ አይላትም፣ ጊዜዋን የምሻማበት ስለሚመስላት ግንኙነታችንን አትወደውም። እኔ ደሞ የፍቅረኛዬ ነገር አይሆንልኝም  ሳላያት፣ ሳልዳስሳት፣ ሳልነካካት  መዋል አይታሰብም። ከባለቤቴ ተደብቄ ከርሷ ጋር አሳልፋለሁ፣ በደስታ እሰክራለሁ፣ በሀሴት እዋኛለሁ፣በሰመመን እዋጣለሁ።ከሷጋር የምለያየው ባለቤቴን እንዳይከፋት ስል ብቻ ነው። አንዳንዴ አሁንስ በዛ ብላ ከእጄ ነጥቃ ምግብ ቀርቧል፣ ቡና ደርሷል፣ ብቻህን እኮ አይደለህም፣ እያለች ስትነጫነጭና ስትቆጣ ፣ ፈገግ ብዬ እጇ ላይ ያለውን በፍቅር የወደኩላትን መጽሀፌን በአይኔ እያየሁ ከተቀመጥኩበት እነሳለሁ። ማንበቤ ከብዙ ነገር ታድጎኛል፣ ቤቴ እንድሰበሰብ አድርጎኛል፣ ትዕግስትና መረጋጋት አጎናጽፎኛል። ለዚህ ነው ከመጽሀፍ ፍቅርየያዘኝ፣  ከንባብ ትርፍ ስለተጠቀምኩ።

Related Articles

እንደ ፍቅር ያለ አስተማማኝ ጥላ የለም

በፍቅር መኖር እረፍት ይሰጣል። ማጣትን ያስረሳል። ፍቅር ያለው ባለው ነገር ይረካል ፣ባለው ነገር ሌሎችን ያገለግላል፡፡ኑሮዬ ይበቃኛልን ያውቃል። በፍቅር የሚኖር የትላንት ማንነቱን አይረሳም፣ ዋጋ የከፈሉለትን ባለውለታዎቹን…

ለዚህ ነው ማንበብ የሚያስደስተኝ፣ አንባቢ ሰው የሚያስቅቀናኝ፣ መጽሀፍት የሚያጓጉኝ!!!

አንባቢ ሰው አንባቢ ሲናገር አይደነቃቀፍም፤ ሃሳብ አይነጥፍበትም። እንዲያውም ቃላት ለሃሳቦቹ ይሰግዳሉ። ቋንቋ ይታዘዘዋል። የቃላት ሃብቱ ንግግሩ በጉጉት እንዲደመጥ ይጎተጉታሉ። አንባቢ ሰው ትልቅ የሃሳብ ጎተራ አለው።…

የማንበብን ትርፍ እረዳለሁ።

የማንበብን ትርፍ እረዳለሁ። በህይወቴዙሪያ ያተረፍኩት፣ በስብዕና ደረጃ የገነባሁት ማንነት ያስደንቀኛል። ከማንበብ  ትልቁ ጥቅሞች አንዱ የመዝናኛ ጊዜዎን የሚያሳልፉበት ውጤታማ መንገድ ነው።ጊዜዎን በዋዛ ፈዛዛ አያባክኑም፣የጊዜ አጠቃቀሞ ይሻሻላል።ማንበብ…

Responses