ከማንበብ አንራቅ
ስናንብ ሙያችን ይሻሻላል፣ ንግግራችን ይዋባል፣ የአስተሳሰብ አድማሳችን ይሰፋል። በማንበባችን ሀሳብ አያጥረንም፣ተጫዋችና ተግባቢ እንሆናለን፣ ከሰዎች ጋር ስንገናኝ ባይተዋር አንሆንም፣ ፍላጎታችንን መግለፅ፣እቅዳችንን ማብራራት፣ ይዋጣልናል። ጥሩ ተናጋሪ እንሆናለን። በማንበባችን መቼ መናገር፣ መቼ ዝም ማለት እንዳለብን እንገነዘባለን። ስናነብ ሰዎች እንዳላዋቂ ቆጥረው አያሞኙንም፣ መፈራታችና መከበራችን ይታወጃል። በሰዎች ዘንድ አንቱ የምንሰኝበትን ገፀሰብ እንላበሳለንና በየዕለቱ በጥቂቱም ቢሆን ከማንበብ አንራቅ። ማንበብ ብቁና ንቁ ያደርጋል መልዕክታችን ነው።
Responses