አእምሮ ልክ እንደ ጎራዴ ነው
ማንበብ እወዳለሁ ማለት አልወድም። ሃሳቤን በምልአት አይገልጽልኝም። ለምሳሌ መተንፈስ እወዳለሁ አትሉም። መተንፈስ ህይወት ነው። ንባብም ለኔ እንዲሁ ህይወት ነው። የማነበው ሲመቸኝ፣ ደስ ሲለኝ አይደለም። የሚመቸኝ፣ ደስ የሚለኝ ሳነብ ነው። የማነበው ከሌላ ጉዳይ በተረፈኝ ግዜ አይደለም። የማነበው በዋና ግዜዬ ነው። ማንበብ ጉዳዬ ነው። የኔ ጉዳይ አንቺ ነሽ ብሏል ዘፋኙ። የኔ ጉዳይ ግን ንባብ ነው። በአጭሩ ንባብ በግድ ሳይሆን በፍቅር የምከውነው ተግባር ነው።
ሳነብ በአእምሮዬ የተደበቁ ቆሻሻ ሀሳቦች፣ ይነፃሉ፣ “አእምሮ ልክ እንደ ጎራዴ ነው። ጎራዴ በሞረድ ካልተሳለ እንደሚዶለዱመው ሁሉ አእምሮም በመጻሕፍት ካልተሳለ ይደንዛል።
ያልሰለጠነ አእምሮ ሃሳብ አይቋጥርም። መፍትሔው በተመረጡ መጻሕፍት አእምሮን መሳል ነው። ንባብ ቢሰለቻችሁ፣ ቀለም አልዘልቀኝ አለ ብላችሁ ማንበባችሁን አታቋርጡ። ቆሻሻው መታጠብ፣ ዱልዱሙ መሞረድ አለበት።
Responses