በቀላል አልተገነባም!!!!
በንባብ ያዳበርኩት፣ በምክርም ያጸናኹት እውቀት እንዲሁ በቀላል የገነባሁት ልምምድ አይደለም። ለእኔ ስነልቦና መገንባት፣ ለነገሮች ያለኝ ክብደት ሚዛኑን የጠበቀ ያልተጋነነና ያልተዛባ እንዲሆን ማድረግ የቻልኩት፣ የሰዎችን ልክ ማወቄ፣ የራሴንም ክብር ማስጠበቄእንዲሁ በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ማንበብ በሕይወት የተፈተንኩበት፣ ከሰው የተገለልኩበት፣ ቢሆንም ባገኘሁት ጥልቅ የህይወት ዘይቤን የመረዳት ሚስጥር አትርፌበታለሁ።የቡና ስብሀቱ መፋጀቱ እንደሚባለው የማንበብ ትሩፋቱ አይን ገላጭነቱ ብዬ በማንበብ ራሳችሁን ፈልጋችሁ አግኙ የዕለቱ መልዕክታችን ነው።
Responses