ማንበብ መንገድ ነው።
ማንበብ መንገድ ነው። መድረሻው የብርሃን ልብ፣ አስተዋይ አእምሮ ነው። መማርህ እንዲህ ካላደረገህ ተወው ይቅርብህ። ማወቅህ ለክፋትህ መሳሪያ ከሆነ አትጠጋው። የአእምሮ እውቀት በልብ ጥበብ ካልተገራ ሁሉም ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ ነው። አእምሮ መሳሪያ ልብ ደግሞ ባለቤት ነው። ልባችን በሚመራን በዚያ መንገድ አእምሮአችን ያድርሰን።
እውቀት በጥበብ ልጓም ካልተበጀለት ግን በዚያ ከፍተኛ አደጋ አለ! ሁሌም ቢሆን አለም የምትታመሰው ልባቸውን፣ ሰብአዊነታቸውን ችላ ብለው አእምሮአቸውን ብቻ ባሰለጠኑ ክፉ ሰዎች ነው። ታሪኩ ትላንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ይኼው ነው። እራሳችንን ሳንለውጥ አለምን ብንለውጥ ድካማችን ሁሉ ረብ ቢስ ነው።
መለወጥ ከራስ ይጀምራል።
ታዋቂው ህንዳዊ ፈላስፋ ኦሾ
Responses