ልምዳችንን እንፈትሽ!
የትኛውም ልምድ እስኪጀመር ይከብዳል። ንባብም እንዲያነው ከዚያማ ተፈጥሮን እስኪያሽር ይፀናል። ስለዚህ ወስን። በየቀኑ የምትወስናቸው ትናንሽ ውሳኔዎች የነገ መድረሻህን ይወስኑታል። ማንበብ ውሳኔ ነው፤ ስፖርት መስራት ውሳኔ ነው፤ በጠዋት መነሳት ውሳኔ ነው፤ ለህይወትህ ከሚጠቅሙህ ሰዎች ጋር መዋልም ውሳኔ ነው። ተኝቶ መዋልም ውሳኔ ነው፤ ብር ማጥፋትም ውሳኔ ነው፤ ቲቪ እያዩ ማምሸትም፣ ፊልም በማሳደድ እና ስልክ ላይ ተጥዶ ጊዜን ማባከንም ውሳኔ ነው። እጅህን ወደ ውሀው ወይ ወደ እሳቱ መስደድ ያንተ ምርጫ ነው! ግን አስብና የሚጠቅምህን ወስን። እኔ ግን እላለሁ ማንበብን የመሰለ ትክክለኛ ውሳኔ አታገኝም። ስታነብ ትነቃቃለህ፣ አቅምህን ታቃለህ፣ የደረስክበትን ትረዳለህ፣ የምትደርስበትን ታያለህ። ስለዚህ እርካታ ያለው ኑሮ መኖር ካለብህ ለማንበብ ወስንና እያንዳንዷን ቅፅበት ተጠቀምባት። EYOB BOOKS HAWASSA ሎጊታ አሮጌ ስታዲየም ስፖርት መሸጫ ሱቆች ላይ እንገኛለን። 0968095969
Responses