ህይወት በማንበብ ትዋባለች፣ ታብባለች፣ ትፈካለች።

ህይወት የምትሸነፈው በትምህርት ብዛት ወይም ረቂቅ እውቀቶችን በመረዳትብቻ አይደለም። ኑሮን የተሻለ ለማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ እራስን የተሻለ አድርጎ መገኘት ነው። በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በስነልቦና፣ የአላማ ሰው በመሆን የተሻለ ሆኖ መገኘት።ለዚህ ደሞ ቁልፉ ማንበብ ነው። ህይወት በማንበብ ትዋባለች፣ ታብባለች፣ ትፈካለች። ሕይወት ውብ እንድትሆን፣በመለወጥ መንገድ እንድትጓዝ ምርጫችሁን አስተካክሉ።

የምትውሉበትን አካባቢ ስትለውጡ ፣ የምታዩትን ማሕበራዊ ሚዲያ ስትለውጡ ፣ የምትይዙትን የቅርብ ጓደኛ ስትለውጡ ፣  የምታነቡትን መጽሐፍ ስትለውጡ ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡በየቀኑ በመደጋገም የምታደርጓቸውን ልማዶች ስትለውጡ  ሕይወታችሁ መለወጡ አይቀርም፡፡

ራሳችሁ የማይሆን ምርጫ  እየመረጣችሁ የማይሆን ሕይወት ውስጥ ስትገቡ ብትነጫነጩ  ምንም አታመጡም፡፡ስለዚህ የለውጡ መንገድ የማንበብ ምርጫ መፍቀድ ነው። መጽሀፍትን መወዳጀት ነው። ከእናንተ የህይወት አላማ ጋር የሚሄዱትን መርጣችሁ አንብቡ፣ ተለወጡ። የዕለቱ መልዕክታችን ነው።

Related Articles

እንዲህ አነባለሁ!

እንዲህ አነባለሁ! • በራእዬ እና በምከታተለው ዓላማዬ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ! • የእኔን፣ የቤተሰቤን፣ የንግዴን፣ የመስሪያ ቤቴንና የሃገሬን ሁኔታ በሚያሻሽል ርእስ ዙሪያ ዘወትር አነባለሁ! • ያነበብኩትን…

በቀላል አልተገነባም!!!!

በንባብ ያዳበርኩት፣ በምክርም ያጸናኹት እውቀት እንዲሁ በቀላል የገነባሁት ልምምድ አይደለም። ለእኔ  ስነልቦና መገንባት፣ ለነገሮች ያለኝ ክብደት ሚዛኑን የጠበቀ ያልተጋነነና ያልተዛባ እንዲሆን ማድረግ የቻልኩት፣ የሰዎችን ልክ ማወቄ፣ የራሴንም…

Responses