ንስርና ምስር

A Book By - ቴዎድሮስ መብራት

In Stock

ንስርና ምስር

Available Book Type

|

|

📗Printed

Book Info

Author - ቴዎድሮስ መብራት

Category -

Publisher - Demo 4 Related Digital Book Publisher

Translated Book - No

Language - Amharic

Translated From -English, English

Number of Pages - 250

Book Review

“…እስካሁን ካነበብኳቸው የወግ መጽሐፎች ይሄኛውን የተለየ ነው እንድል ከሚያደርጉኝ ነገሮች መካከል የተመጠነ፣ የተወሰነ፣ እዛ እና እዚህ ሳይዝረከረክ፣ ሳይዝረበረብ ስለአንድ ርዕሰ ጉዳይ [የዩኒቨርሲቲ ሕይወትን] በሚያውቀው ልክ ለማብራራት እና ለመተንተን መቻሉ ነው።
… መጽሐፉ የወግ ስብስብ ነው። እነዚህ ወጎች ለየብቻ ራስ ራሳቸውን ችለው የቆሙ ናቸው። በጋራ ሲታዩ ደግሞ ይናበባሉ፣ ይዛመዳሉ፣ ይዋደዳሉ ሁሉም የሚያወራው የዩኒቨርሲቲ ሕይወትን ስለሆነ።
… ወጎቹ አንዴ ተኮሳትረን፣ አንዴ ፈገግ ብለን የምናነባቸው ከራሳችን ጋር የሚያጨዋውቱንና የሚያነታርኩን ናቸው። ሆኖም እያንዳንዱ ወግ መጣጥፍ ውስጥ ተመላልሶ የሚመጣ አንድ ዜማ አለ። ዜማው አዝማች አለው። አዝማቹ ደግሞ ሀገር ነው። ሀገሪቷ ኢትዮጵያ ናት። ደራሲው ኢትዮጵያ ህመሙ እንደሆነች ነው የምታዩት።”
ደራሲ ዶ/ር እንዳለጌታ ከበደ (ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ.ም መጽሐፉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲመረቅ ከተናገረው የተወሰደ)

“…የቴዎድሮስ መብራት ‘ንሥር እና ምስር’ የሚለውን በዩኒቨርሲቲ አጸድ ውስጥና በአፍአም በዙርያው ስላለ ሕይወት የሚተርከውን መጽሐፍ በየትኛውም እድሜ የሚገኙ ሰዎች ሊያነቡት ተገቢ ብቻ ሳይሆን ግዴታም መስሎ ይሰማኛል።
አዛውንቶች ትዝታቸውን ለማመንዠክ፤ ወጣቶች ትላንትናቸውንና መጪውን ለመረዳትና ለመጓጓት ጭምር።
ልጅህን፣ ወንድምህን፣ እህትሽን፣ ጎበዝ ተማሪ እንድትሆን በምክር ሰበብ አትጨቅጭቃት፣ አትጨቅጭቂያት ‘ንሥር እና ምስር’ የሚለውን መጽሐፍ እንድታነብ ስጦታ ስጫት፣ስጣት። ምንን መጠንቀቅና ምንድን ማድረግ እንዳለባት ተዋዝቶ ታገኘዋለች። ዩኒቨርሲቲ አለመግባት ከሕይወት ገፅ መሰረዝ መስሎ እስኪሰማት ድረስ።
ቴዎድሮስ መጽሐፉን እንደ ንሥር አራቅቆ፣ እንደ ምስርም ተጠንቅቆ የሠራው መጽሐፍ ለመሆኑ ምስክርነቴን አንብበውና እመነው!”
ደራሲ፣ ገጣሚ እና ባለቅኔ ኤፍሬም ሥዩም (ሶሊያና) Jun 15 2022 (ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም) በፌስቡክ ገጹ ላይ የጻፈው።

Digital/Audio Book Files

    Br500.00

    The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.

    The book is available for borrowing. Select the number of days** the book can be borrowed. Standard borrowing duration is 7 days.
    Product total
    Options total
    Grand total
    -
    +

    “….እንደ እኔ እምነት! ሰው የሚሠራው ገና ከማሕፀን ነው። የሚያድገው በወላጅ፣ በጎረቤት፣ በመንደርና በአካባቢ ጭምር ነው። በዐየው፣ በሰማው እና በተገነዘበው ልክ ይቃኛል። ጠያቂ ሞጋች ሆኖ ለመገኘትም ሆነ በተሠራው ልክ ለመብቀል ዕድሉ ያለው በሌሎች ነው። ስለዚህ ትውልድ እንዴትም ሆኖ ቢሠራና ቢገኝ እንደዘሩት መብቀሉ፣ እንደሠሩት መገኘቱ የእጣ ፈንታ ጉዳይ አይሆንም። ዛሬ ትውልዱ ሆኖ ለተገኘውም ሆነ ሊሆን ላሰበው ሁሉ ትናንቱ እና ቀዳሚው ትውልድ የሠራው ሥራ ዋና ተግባር ነው። በዚህ ሥራ የምናያቸው የተበራከቱ የሥነ ልቡና እና የሥነ ምግባር ድቅቀቶች የመጡት በዛሬዎቹ የጥፋት ሰለባዎች እሺታነት ሳይሆን በትናንቶቹ የጥፋት መልዕክተኞች የሕሊና እና የሞራል መንጠፍ ነው። ሀገርን በዋና ሞተርነት የሚረከባት ትውልድ የተማረው ኃይል ነው። ዘመኑን የዋጀ፣ ተወዳዳሪ እና ተፎካካሪ ትውልድ የሌላት ሀገር እርምጃዋ በዚያው ልክ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። በንሥርና ምስር መጽሐፍ ውስጥ በዘመኑ የተማረውን ትውልድ እንድናየው ስንታገዝ ጥቂት የሚባሉ እና የነገዋን ሀገር የጀርባ አጥንት የሚሆኑ ልሂቃንን በጭላንጭል እንድናይም ቀጭን የማርያም መንገድ ሰጥቶናል።”
    ዶ/ር አንዱዓለም አባተ (የአጸደ ልጅ)
    የሥነ ጽሑፍ፣ የቴአትር እና የፎክሎር ተመራማሪ

    You May Also Like