ጠበኛ እውነቶች
A Book By - ሜሪ ፈለቀ / Merry Feleke

In Stock
ጠበኛ እውነቶች
Available Book Type
|
|
Book Info
Author - ሜሪ ፈለቀ / Merry Feleke
Category - ልብወለድ
Translated Book - No
Language - Amharic
Number of Pages - 252
Book Review
“ጠበኛ እውነቶች” በ4 ክፍሎች የተከፈለ ልብወለድ ሲሆን፤ የተለያየ ማህበራዊና ግላዊ ሕይወትን የሚዳስስ መፅሐፍ ነው።
መጽሐፉ በ252 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን፤ በውስጡ የተካተቱ አራቱ ታሪኮች፡- “ቅዳሴና ቀረርቶ፣ ቀላውጦ ማስመለስ፣ እናቴን ተመኘኋት፣ ምርጫ አልባ ምርጫ” ይሰኛሉ ::
Digital/Audio Book Files
Br350.00
The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.
ጥላቻ የሚያምር ነገር መሆኑን አላውቅም፡፡ ጥላቻን የተሸከመ ልብ ንፁህ መባሉም አይገባኝም፡፡” አልኳት::
“አያምርም፡፡ አዎን ጥላቻ አያምርም፡፡ አየህ እውነትህን? ሁሉም ሰው በልቡ ለማንም ማሳየት የማይፈልገው ቆሻሻ ይኖረዋል፡፡ ᎙_ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ግልፍተኝነት፣ ራስን መውደድ….. አንዱ በነነ ይኖርበታል፡፡
ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባሕሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎ ካልተገለጠ በስተቀር ንጹሕ፣ ቅን እና ሁኔታ እንደሆንን እናስመስላለን፡፡ አንተ እንደዛ አይደለህም፡፡
የተሰማህንና የሆንከውን ብቻ ነው የምትኖረው፡፡ የኖርከው ሕይወት የፈጠረብህን ጥላቻና ሽሽት አትደብቀውም፡፡ ያ ደግሞ እንድትድን ያደርግሃል። አንተ ክፉ ልብ የለህም፡፡ ማንንም መጉዳት አስበህ አትጎዳም።