ግርባብ

A Book By - ፍቃዱ አየልኝ/ Fikadu Ayelign

In Stock

ግርባብ

Available Book Type

|

|

📗Printed

Book Info

Author - ፍቃዱ አየልኝ/ Fikadu Ayelign

Category -

Publisher - walia books

Translated Book - No

Language - Amharic

Number of Pages - 237

Book Review

ግርባብ የልቦና ውቅራችንን ከሌላ ማዕዘን የሚፈትሹና ታላቅ ቁም ነገርን የሚያትቱ ተረኮችን የያዘ ነው፡፡ በሳል ደራሲ ልቦናችን ያልደረሰበትን እውነት ከሌላ ማዕዘን ገልጦ የሚያስቃኝ ነው፤ ማለፊያ ድርሰትም በብዙ ትርክት የገነባነውን ርዕዮት እንድንከልስ እጅ የሚያሰጥ ነው፡፡
ግርባብ ውስጥ የቀረቡ የአጭር አጭር ተረኮች (flash fictions) በሁለተኛ መደብ፣ በሦስተኛ መደብ አዋቂ ኩሉ እና በተውኔታዊ የትረካ አኳያ የተነገሩ ናቸው፡፡
ኪናዊ ይዘቱ ከፍ ያለ ድርሰት የሆነው ግርባብ፤ ደልዳላውን የህላዌ ፍኖት አመላካች ነው፡፡ ቁርቁዝና የጋረደብንን ሰፊ ዓለም የሚያሳይ ፋና ነው፡፡ ኑሮን ለማቅናት የሚገበዩ ጥበባት ቋት ነው፡፡ ከወል የግብረ ገብ እሴት እግር ብረት የምንላቀቅበት የአርነት መንገድ ነው፡፡
ግርባብ በውብ ቋንቋ የተከተበ ድርሳን ነው፡፡ የደራሲው የቃላት ግልጋሎት ከሚያትተው ጉዳይ አውድ ጋር የተዛነቀ ነው፡፡ በሳል ደራሲ በጽሑፉ ቃላትን ያለ ቦታቸውና ያለ አንድምታቸው አይሰገስግም፡፡ በተጨማሪም፣ ደራሲው በዐሳቦች ላይ በጥልቀት እንድንብሰለሰል ይኮረኩረናል እንጂ አይሰብከንም፡፡ የደራሲው እያንዳንዱ ነጠላ ዓረፍተ ነገርም ለሰፊ ትንታኔ የሚጋብዝ ዐሳብን የተሸከመ ነው፡፡
ግርባብ ውስጥ ተሰንደው የቀረቡ የአጭር አጭር ትረካዎች፣ አንዳንዶቹ በታሪክ የተዛመዱ ናቸው፡፡ አንዱ ትረካ ውስጥ የተወሳው ጭብጥ ሌላ ትረካ ውስጥ በጥልቀት ተተንትኖ፣ አዲስ መነፅር ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ግርባብ ዓለም ባበጀው የመደብ ተዋረድ (class hierarchy) ታችኛው እርከን በሚገኙ ተራ ሰዎች ህላዌ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው፡፡ ደራሲው ከሳለቸው ገጸባሕርያትም ጥቂቶቹ ገበሬ፣ አናጺ፣ እረኛ፣ አንጥረኛ፣ ጠራቢ፣ ብራና ፋቂ፣ ጫማ ሰፊ፣ ቆብ ሠሪ፣ ሹፌር፣ ድንጋይ ፈላጭ፣ አዝራር ሠሪ፣ ግንበኛ፣ ሸክላ ሠሪ፣ ልብስ ሰፊ፣ መስታይት ሠሪ፣ ሰዓት ሠሪ፣ ቀለም ቀቢ፣ ኩራዝ ሠሪ፣ ቆዳ አቅላሚ፣ ጨው ነጋዴ፣ ወረቀት ሠሪ፣ ሚዛን ሠሪ፣ በር ሠሪ፣ ሽንኩርት ነጋዴ፣ እንቁላል ነጋዴ፣ ዘበኛ እና ድንጋይ ፈላጭ ናቸው፡፡ በተጨማሪም፣ ድርሰቱ ከሰዎች ሌላ እንሰሳት እና እፅዋት ገጸባሕርይ ሆነው የተሳሉበት ነው፡፡ እነዚህ ገጸባሕርያት ተምሳሌታዊ (metaphorical) ናቸው፡፡
ግርባብ ያልቃኘው፣ ያልመረመረው የነገረ ሰብዕ ጉዳይ የለም፡፡ ፍልስፍናዊ፣ መለኮታዊ፣ ሥነ ማኅበረሰባዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጉዳዮች የድርሰቱ ዐቢይ መሽከርከሪያዎች ናቸው፡፡ ድርሰቱ በእነዚህ ዐቢይ ጽንሰ ዐሳቦች ሥር የሚካተቱ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን ዳስሷል፡፡ ከእነዚህ መካከል ጥቂቶቹ ጽድቅ እና ኩነኔ (good and evil)፣ ቀንበር እና አርነት (oppression and freedom)፣ መነጠል እና አብሮነት (isolation and intimacy)፣ መከራ እና ደስታ (tragedy and happiness)፣ ግብዝነት (persona)፣ ህብረት (unity)፣ ደግነት (generosity)፣ ኑባሬ (existence)፣ ራስ (self) እና ጊዜያዊነት እና ዘላቂነት (temporality and eternity) ናቸው፡፡
ግርባብ በዛ ባሉ የድርሰቱ ታሪኮች ውስጥ ዐቢይ ገጸባሕርይ (protagonist) ሆኖ የተሳለውን ደግ ሰው ስንክሳር በውብ አተራረክ የሚያስቃኝ ድርሳን ነው፡፡ ይህ ሰው ጥበብ ሐሣሽ፣ መርማሪና ጠያቂ ነው፡፡ የሚያነሳቸው ተጠየቆች አድማሳችንን አስፍተን ኑባሬን በጥልቀት እንድንመረምር የሚጋብዙ ናቸው፡፡

Digital/Audio Book Files

    Br500.00

    The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.

    The book is available for borrowing. Select the number of days** the book can be borrowed. Standard borrowing duration is 7 days.
    Product total
    Options total
    Grand total
    -
    +

    ግርባብ በእዚህ መጣጥፍ ያላወሳኋቸው አያሌ አመራማሪ፣ ሞጋችና አጫዋች ዐሳቦች የተካተቱበት ማለፊያ የፈጠራ ሥራ ነው፡፡ ፍቃዱ የራሱን አሻራ ያተመበት ይህ ድርሳን፤ የሀገሪቱ ሥነጽሑፍ እምርታ እያሳየ ስለ መሆኑ ማስረገጫ ሆኖ የሚቀርብ ነው፡፡
    ከአዘጋጁ፡-
    መኮንን ደፍሮ ልብወለድ ጸሐፊ፣ ገጣሚና የሥነ ጽሑፍ ኀያሲ ነው፡፡