መንግሥቱ ኃ/ማርያም፡ የሥደተኛው መሪ ትረካዎች
A Book By - ይታገሱ ጌትነት ገበየሁ/ Yitagesu Getinet Gebeyehu

In Stock
መንግሥቱ ኃ/ማርያም፡ የሥደተኛው መሪ ትረካዎች
Available Book Type
|
|
📗Printed
Book Info
Author - ይታገሱ ጌትነት ገበየሁ/ Yitagesu Getinet Gebeyehu
Category - History
Publisher - walia books
Translated Book - No
Language - Amharic
Book Review
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በአዎንታም ይሁን በአሉታ ጉልህ ድርሻ ያላቸው ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያምን ደራሲና ገጣሚ ይታገሱ ጌትነት በሀራሬ መኖሪያ ቤታቸው ተገኝቶ ያደረገላቸውን ቃለመጠይቅ መሠረት በማድረግ ያሠናዳው መጽሐፍ ሊወጣ ነው፡፡
መጽሐፉ የቀድሞው የኢትዮጵያን ፕሬዝዳንት ኮ/ል መንግሥቱ ከልጅነት አንስቶ ዛሬ እስካሉበት የስደት ዘመን ድረስ የተጓዙባቸውን ግላዊ ታሪኮች፣ የሕይወት ገጠመኞች እና ወቅታዊና ነባር ፖለቲካዊ ግምገማዎችን አካትቶ ይዟል፡፡ መጽሐፉ ዐቢይ ትኩረቱም እንደሰው የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ማንነነት መመልከትና ያልተደመጠውን ድምጽ መሥማት ሲሆን፣ እጅግ በርካታ ያልተነገሩ ታሪኮችን የያዘ ነው፡፡
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ቁምነገሮች ለታሪክ አጥኚዎች ግብአት፣ ለከያንያን የመነሻ ሀሳብ፣ ለፖለቲከኞች ትምህርት፣ ለጋዜጠኞች መረጃ፣ ለወጣቶች የሕይወት ልምድን፣ እንደሕዝብም ካለፈው በጎም ይሁን መጥፎ ታሪክ ለመማር ለሌሎችም እንደሙያቸውና ማንነታቸው የሚወስዱት ቁምነገር አያጡበትም ሲል የመጸሐፉ አዘጋጅ ይታገሱ ገልጿል፡፡
ይታገሱ ጌትነት ከዚህ ቀደም “ጥቁር ነጥብ”፣ “ደጅ ያደረ ልብ” እና “የደመና መንገድ” በተሰኙ መጸሕፍቶቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ በበርካታ የሥነጥበብ እና የመጽሐፍ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን እና ትንታኔዎችን በማቅረብ ይታወቃል፡፡ ደራሲና ገጣሚ ይታገሱ ጌትነት የቀድሞው ሕጻናት አምባ ካፈራቸው ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ የመጽሐፉ አሳታሚና አከፋፋይ አራት ኪሎ ኢክላስ ሕንጻ ላይ የሚገኘው ዋሊያ መጥሐፍ መደብር ሲሆን፣ ከፊታችን ቅዳሜ አንስቶ በሁሉም የመጽሐፍ መደብሮችና አዟዎሪች እጅ ይገኛል፡፡
#ቅምሻ_ኃይለ_ቃል!
“ሁሉም ሊረዳው እንደሚችለው፣ “. . . . .” ብለን የከፈልነው መስዋዕትነትና ተጋድሎ እራሱን የቻለ ልዩ ታሪክ ሆኖ አልፏል። ይኽ ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል። ይኽንን ሲወያዩት የነበሩት ጓደኞቼ ሁሉም (በአብዛኛው) በሕይወት የሉም፤ ይኼንን መራር ታሪክ ብቻዬን ሳወጣ ሳወርድ እኖራለሁ። የማያስደስት ታሪክ . . . በአንደዳንድ መልኩ የሚያስለቅስም ነው። “የትላንቱ ግድ የለም ለሀገር ተብሎ ይኼ ሁሉ ተከፍሏል፤ ነገ ምንድነው ተስፋችን?” ብዬ ስጠይቅ ተስፋ አይታየኝም። ምንአልባት ተሳስቼ ሊሆን ይችላል። “ኢትዮጵያ ሊመጣባት የሚችለውን ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ችግር የሚቋቋም ማዕከላዊ ፎርስ ማን ነው? ለአንድነቷ፣ ለሰላሟ” ብዬ ስጠይቅ መልስ የለኝም። ይኼው ነው!”
Digital/Audio Book Files
Br596.00