እመጓ
In Stock
እመጓ
Available Book Type
|
|
Book Info
Category - Mystery
Translated Book - No
Language - Amharic
Book Review
“እመጓ” ዐለም አቀፍ ጥንታዊ ቅርስ ሰሜን ሸዋ መንዝ ውስጥ መኖሩን ሰምተዋል? ወልፍራም የተባለው ደራሲ ፓርዚባል በተባለው ድርሰቱ የተናገረለት ቅዱስ ጽዋ (Holy Grail) ምን እንደሆነና የት እንዳለ ያውቃሉ? እንግዲያውስ እመጓን ያንብቡ፤ መልሱን ያገኙታል፡፡
Digital/Audio Book Files
Br280.00
The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.
እመጓ የእኛ ዘመን ዘመናዊ ትውልድ የደረሰበትን የባህል ግጭት ማዕከል አድረጎና ቀዳሚው የሕይወት ፍልስፍናችን ከአዲሱ የሰው ልጅ የቴክኖሎጂ እድገትና ውስብስብነት ጋር ከመስማማት አልፎ ሚያመጣውን ችግር የማስወገድና የማከም አቅም ያለው መሆኑን ለማሳየት የተዘጋጀ ሚታዊ ድንቅ የጉዞ ልቦለድ መሆኑን ለመረዳት የሚያዳግት አይመስልም፡፡ በተለይም ጽዋው መንዝ ውስጥ እመጓ ይገኛል ብሎ ሲሳይን በዚሁ አሳምኖ መጨረሱ መጽሐፉ አንደኛ በአንጻረ ጽዋ የሕይወት መገኛዎች (ለምሳሌ እነ አባ አክሊሉ ዓይነት ሰዎች) ያሉት እዚህ ነው፤ ማዕከሉም (መንዝ ለኢትዮጵያ ማዕከል እንደምትሆነው) እዚሁ ነው፤ መንዝህ የሕይወት መርጫዉም፣ ተረጭውም፤ ረጪውም፣ የሚረጨውም እዚሁ ነው፡፡ እመጓ – እመ እጓል ፡- የልጆች እናትም ኢትዮጵያ ናት፤ ሌላው ከእንጀራ እናትነት አያልፍም የምትል ለኢትዮጵያ ከተሜ ትውልድ ፈውስነት የቀረበች የአእምሮ ማረጋጊያ (Mental Therapy) ትመስለኛለች፡፡ ሆኖም መጽሐፉ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ያለውን ቦታና ማኅበረሰባዊ ተጽእኖ ለማየት ገና ገና ሰፊ ጥናትና ምርምርን የሚሻ ድንቅ መጽሐፍ

