-
admin Reading Really Matters! posted an update
5ኛ ዓመት 14ኛ ዙር ሀዋሳ ታነብባለች የከተማችን የንባብ ባህል ማበልፀጊያ የመጽሀፍት ኤግዚቢሽንና ባዛር ከዛሬ ሐምሌ 5 – ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን ድረስ ሲዳማ ባህል አዳራሽ ፊት ለፊት አዳዲስ መጽሀፍትን ከ20-40% ቅናሽ በማድረግና የቆዩ ተፈላጊና አሮጌ መጽሀፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን እንቀርባለን።
ይህ አውደ ርዕይ እንዲሳካ የአንበሳውን ድርሻ የተወጡት ቤቢ ትሬዲንግ ደረጃቸውን የጠበቁ ድንኳኖችን በነፃ በመስጠት አጋርነታቸውን ደጋግመው አሳይተዋል፣ ጠረጴዛዎችን በመስጠት ዘውትር ከጎናችን ያለው ዩኒየን አካዳሚ ሲሆን፣ የአከፋፋዮችን የትራንስፖርትና የማረፊያ ወጪ በመሸፈን በግል እየተጋ የሚገኘው ሰማይመልቲሚዲያ (ኢዮብ ጽጌ) ነው። ለዝግጅቱ መሳካት ሙያዊ ድጋፍና ቀና ትብብር ያደረጉልንን የሀዋሳ ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ባለሞያዎችና የሲዳማ ባህል አዳራሽ አስተዳደር እንዲሁም የክፍለ ከተማው አመራሮች ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
READING REALLY MATTERS!!!!!!