-
Eyob posted an update
· የንባብ ትሩፋት
ንባብ ከዚህ ዓለም ጫጫታ “እፎይታ” ማግኛ ነው። ማንበብ በዚህ ሩጫ በበዛበት ዓለም ውስጥ የነፍስን ረሃብ የሚያስታግስ የጥሞና ጊዜ መውሰጃ፣ ከጥድፊያ የማረፊያ ወደብ ነው። አንዳንዴ ሮጠን፣ ደክመን ስልችት ሲለን ፊታችንን ወደ መጽሀፍት ብናዞር መጽናናት፣ ትዝታ፣ ሳቅ፣ ፈገግታ፣ ብርታት፣ እናገኝባቸዋለን። በንባብ የደከመው አካላችን፣የዛለው መንፈሳችን ይታደሳል፣ የተደበቀብንን የስኬት ሚስጥር፣ የተጋረደብንን የጥበብ መስኮት ይከፍትልናል። ማንበብ የተዘነጋ የለውጥ መንገድን ያመላክተናል፣ የተቀበረ እምቅ እውቀትን፣ ያልተጠቀምንበትን መረጃ ያስታውሰናል። ማንበብ ወደ ነገ ለማየት ሀይልን ያቀዳጃል። እናም ፊታችንን ወደ መጽሀፍት እንመልስ።
ኢዮብ ጽጌ
ሐምሌ 6 ቀን 2016