ብቸኛ መሸሸጊያዬ ናት

እሷ የህሊና ምግብ ሙዳይ ናት። ምንም ብሆን፤ ምንም ባጣ የማይደንቀኝ ልበ ደንዳና እንደሆንኩ ያለፍኩበት ጨለማ ይመሰክራል፤ እሷ ብቻ ከእኔ ጋ ትሁንልኝ እንጂ የትም ይመቸኛል። እሷን ያላገኘሁ ቀን ነው  መንፈሴ የሚታወከው፤ እሷ ካለችበልቤ ሀሴት ሞልቶ እንደተመላለሰ የተሰፈረለኝን ዘመን ጨርሳለሁ።ላንለያይ ተዋደናል።

እሷ የልቤ ብርሃን ናት፡፡ ግፍን እቋቋም ዘንድ የተቸረችኝ ጫንቃዬ ናት፤ በንፅሕና ከእውነት ጋ እንድቆም፤ አቋሜ እንዳይሸረሸር፤  መንገዴንየምትመራኝ የሚስጥር ሙዳይ፣  በፍቅር ˚ ከመንገዴ እንዳልሰናከል በትልቁ አቅም ሆናኛለች፡፡

በጠላትና በአሰናካይ፣ተከብቤ እንዳላፈገፍግ የምታበረታኝ የደስታዬ ፍላጽ ብቸኛ መሸሸጊያዬ ናት። የዓላማዬን ያህል ነው የምወዳት……….መጽሀፌ ጓደኛዬና መምህሬ፣ መካሪዬና መዝናኛዬ፣ ሁሉነገሬ ናት። አንቺ ስላለሽኝ እኔ በኩራት እራመዳለሁ፣ ከእስትንፋሴ እኩል አብረሽኝ ትኖሪ ዘንድ ቃልኪዳን ገብቻለሁ።

Related Articles

እንደ ፍቅር ያለ አስተማማኝ ጥላ የለም

በፍቅር መኖር እረፍት ይሰጣል። ማጣትን ያስረሳል። ፍቅር ያለው ባለው ነገር ይረካል ፣ባለው ነገር ሌሎችን ያገለግላል፡፡ኑሮዬ ይበቃኛልን ያውቃል። በፍቅር የሚኖር የትላንት ማንነቱን አይረሳም፣ ዋጋ የከፈሉለትን ባለውለታዎቹን…

ንባብ አጭር የሆነችውን ሕይወት በረጅሙ ለመኖር የሚረዳ ተመራጭ መንገድ በመሆኑመጽሀፍትን እንመርምር

መጻሕፍት የረቀቀውን አጉልትው የሚያሳዩ፣የተሰወረውን ምስጢር ገልጠው የሚያስረዱ የእውቀትና የጥበብ ምንጮች ናቸው፡፡ይህንን ዘመን-ዘለቅ እውነታ በውል የተገነዘቡት አበው ‹‹ሁሉንም መርምሩ መልካሙን ያዙ›› በማለት አበክረው ይመክራሉ፡፡በምክራቸውም የማያውቁትን በጥልቀት…

ፍቅር የያዘኝ

ባለቤቴን በጣም እወዳታለሁ፣ ለህይወቴ ትርጉም የሰጠቻት እሷ ናት። እኔ ግን ሌላ ፍቅረኛ አለችኝ።ከሷ ጋር ስሆን ባለቤቴ ደስ አይላትም፣ ጊዜዋን የምሻማበት ስለሚመስላት ግንኙነታችንን አትወደውም። እኔ ደሞ…

Responses