ንባብ አጭር የሆነችውን ሕይወት በረጅሙ ለመኖር የሚረዳ ተመራጭ መንገድ በመሆኑመጽሀፍትን እንመርምር
መጻሕፍት የረቀቀውን አጉልትው የሚያሳዩ፣የተሰወረውን ምስጢር ገልጠው የሚያስረዱ የእውቀትና የጥበብ ምንጮች ናቸው፡፡ይህንን ዘመን-ዘለቅ እውነታ በውል የተገነዘቡት አበው ‹‹ሁሉንም መርምሩ መልካሙን ያዙ›› በማለት አበክረው ይመክራሉ፡፡በምክራቸውም የማያውቁትን በጥልቀት መርምሮ፣ መልካም ያሉትን አጥብቆ የመያዝን ጠቀሜታ ይጠቁማሉ፡፡ የማያውቁትን ጠልቆ ለመመርመር፣ጠንቅቆ ለማወቅም ሆነ አጥብቆ ለመያዝ ደግሞ ከንባብ የተሻለ አማራጭ የለም፡፡ለምን ቢባል መጽሀፍትን ማንበብ ማንነትን ከስር ከመሠረቱ ለማወቅ፣አስተሳሰብን ለመቀየር፣ሕይወትን ለመለዋወጥና ባለራዕይ ለመሆን ያስችላልና ነው፡፡
በመሆኑም ዘርፈ ብዙ ጥበብን ለመገብየት የሚተጋ ማንኛውም ሰው (ዜጋ) በተለይ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ/የመጻሕፍትን የእውቀት ማዕድ በመቋደስ አእምሮን ማጎልመስ ይጠበቅበታል፡፡ይህ ሲሆን ብቻ ነው የሕይወት ዘመን ውጥኑን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል የእውቀት አቅም መፍጠር የሚችለው፤ብሎም በእውቀት ላይ በተመሠረተ አኩሪ ተግባሩ የትውልድና የሀገር ተረካቢነት አደራውን በአግባቡ የሚወጣው፡፡ስለሆነም የዛሬው መልዕክት ንባብ አጭር የሆነችውን ሕይወት በረጅሙ ለመኖር የሚረዳ ተመራጭ መንገድ በመሆኑመጽሀፍትን እንመርምር እላለሁ።ኢዮብ ጽጌ ታህሳስ 5
Responses