ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም!!!!
መፃሕፍትን ከማንበብ ባሻገር በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከሃሳባችን ጋር በማስተያየትና በማሻሻል፣ በማሠላሠልና በማስተዋል አዲስ ሃሳብ ካልፈጠርንበት መፅሐፍ ማንበብ ሳይሆን መፅሐፍ መቁጠር ነው የሚሆነው፡፡ ባነበብነው ሃሳብ ተገዝተንና አዲስ የባህሪ ለውጥ ወይም አዲስ ነገር ካልፈጠርንበት ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ዕውቀት ስንል በተጨባጭ በተግባር የሚገለፅ ነውና፡፡ስለሆነም የምናነበውን ከህይወት ዘይቤያችን ጋር አሰናስለን ለተሰማራንበት ሙያ መሻሻልና ራሳችንንም ብቁ ለማድረግ በሚጠቅም መልኩ እናንብብ፣ ያኔ ልዩነት ፈጣሪዎች ሆነን ወደከፍታችን እንወጣለን፣ ስኬታችንን እናጣጥማለን። ኢዮብ ጽጌ ነሀሴ 21,2016
Responses