መጽሀፍት ክቡር ናቸው!
“የህይወታችን ትልቁ ደስታ መፀሀፍ ከማንበብ የሚገኝ ነው ብዬ በድፍረት ላውጅ እችላለሁ።ምክንያቱም መጽሐፍት ዓለምን ሁሉ የቀየሩ የስልጣኔ ዋና ቁልፎች ናቸው። ዓለም እዚህ የደረሰችው መፃሕፍት ታትመው ነው። የሰው ልጅ የዕውቀት ብልፅግና፣ ልዕልና፣ ሃያልነት፣ ግርማ ሞገሱ ሁሉ ከመፃሕፍት ጋር የተቆራኘ ነው። መፃሕፍት ክቡር ነገሮች ናቸው። ውስጣቸው ዕውቀት አለ፣ ሰው አለ፣ ታሪክ አለ፣ ፈላስፋ አለ፣ ሊቅ አለ፣ ፈጣሪ አለ፣ ኧረ ምን የሌላ ነገር አለ?
Responses