ፍቅር እስከ መቃብር

A Book By - ሀዲስ አለማየሁ

In Stock

ፍቅር እስከ መቃብር

Available Book Type

|

|

📗Printed

Book Info

Author - ሀዲስ አለማየሁ

Category -

Publisher - ማንኩሳ

Translated Book - No

Language - Amharic

Number of Pages - 552

Book Review

በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የቀረበ ልብ ወለድ ሲሆን ሰብለ ወንጌል እና በዛብህ የሚባሉ የሁለት ገፀ ባህሪያን ፍቅር ላይ ያተርኩራል። ሀዲስ ዓለማየሁ “ፍቅር እስከ መቃብር” በተሰኘው የአማርኛ ረዥም ልቦለድ ሥራቸው “ለኢትዮዽያ ሥነጽሁፍ አዲስ ምእራፍ ከፋች” የሚል ሞገስ ያገኙ ሲሆን፣ በዚሁ ኪናዊ ሥራቸውም ፋሽስት ኢጣሊያ ከወጣ በኋላ ብዚዎቹ ኢትዮዽያውያን ደራስያን ያላተኮሩበትን የፊውዳል ኢትዮዽያን ገፅታ በተለየ ትኩረት በስፋትና በጥልቀት በመዳሰስ ኪናዊ በሆነ የቋንቋ ኃይልና ውበት የገለጹ፣ በፊውዳሉ ሥርዓት ላይ ያመፁ እንደ ጉዱ ካሣ፣ በዛብህ፣ ሰብለወንጌል፣ አበጀን የመሳሰሉ ሕይዋን ገፀ ባሕርያት በመሳል- በለውጥ የትግል መንፈስ ላይ ለነበረው አዲስ ትውልድ ሀዲስ ራዕያቸውን በጥበብ አጋርተዋል። በአጻጻፍ ብልሃቱ በአማርኛ ሥነ ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ አዲስ ፈር በቀደደው የ”ፍቅር እስከ መቃብር” ድርሰታቸው በሁለት የውጭ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። ደራሲ ሐዲስ አለማየሁ የኖሩበትን የፊውዳሉን ዘመን ባህል፣ አስተሳሰብ እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ በዘመኑ ያልተፈጠረን አንባቢን ጭምር በምናቡ ዘመኑን እየሳለ ያልኖረበትን ዘመን ጣእም እንዲያጣጥም ያስቻለበት ድንቅ የፍቅር መጽሐፍ ነው። በኢትዮጵያ ዘመናዊ የአማርኛ የልቦለድ ስነጽሑፍ ታሪክ በብዙ ጸሐፍት ቁንጮ ስፍራን የያዘም ነው።

Digital/Audio Book Files

    Br500.00

    The price displayed is for purchasing the book. If you choose to buy borrow the book for 7 days, the price will be reduced by 90%. By default, the "Borrow this book" option is selected.

    The book is available for borrowing. Select the number of days** the book can be borrowed. Standard borrowing duration is 7 days.
    Product total
    Options total
    Grand total
    -
    +

    ፍቅር እስከ መቃብር የማይነጥፍ የወርቅ ጉድጓድ ነው። የፊታውራሪ መሸሻ እና የፊታውራሪ አሰጌ፣ የፊታውራሪ መሸሻ እና የአበጀ በለው፣ የሰብለ እና የደንገጡሯ፣ የበዛብህ እና የባልንጀራው እያሉ መቀጠል ይቻላል። ዳሩ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም። ፍቅር እስከ መቃብር ዛሬም በፖለቲካው፣ በማህበራዊው፣ በፍልስፍናው እየገባ እልፍ ትርጉም የሚሰጥ ታላቅ ልብወለድ ነው። ወይ ፍቅር እስከ መቃብር! ግሩም ልብወለድ!