እናነባለን!!!!
እናነባለን!!!
ስለሚያዝናናን
ስለሚያስቀን
ስለሚያስለቅሰን
ስለሚያስደስተን
ስለሚያሳዝነን
ስለሚያወዛግበን
(ተወዛግበን ደግሞ አንቀርም,,,,
አበው በጥበባቸው
ሳይጣመም አይቃናም፤
ሳይደፈርስ አይጠራም ብለው ከመጽሀፍ አስቀምጠውልናልና!)
ህይወታችንን በዚህ ሁሉ ክቡር ስሜት ስለሚሞላልን እናነባለን።
ወደላይ ስለሚያጎነን
ወደታች ስለሚያፈርጠን
ወደኋላ ስለሚስበን
ወደፊት ስለሚገፋን
ከታሪክ ስለሚያስቃኝን
በምናብ ስለሚያንሳፈን
ለዚህ ሁሉ ስንል እናነባለን!!!
ወደ ነፍስ ስለሚያጠልቀን
ወደ አለም ስለሚያሰፋን
ከብቸኝነት ስለሚፈውሰን
ወደ ራስ ስለሚያቀርበን
ወደ ሩቅ ስለሚያስፈነጥረን
እናነባለን!!!
እንደ አባት ስለሚገስጸን
እንደጓደኛ ስለሚመክረን
እንደ ልጅ ስለሚያጫውተን
እንደወረተኛ ስለማይከዳን እናነባለን!!!
እናንተም ኑና አብረን እናንብብ!!! መጽሀፍት ለሁሉም!!!
ከቴዎድሮስ ሸዋንግዛው ገፅ የተወሰደ
Responses