የልጆች የንባብ ፌስቲቫል
የ2016 የትምህርት ዘመን መጠናቀቅን አስመልክቶ ሰማይ መልቲሚዲያ ከሲዳማ ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ቅዳሜ ሰኔ 22 በጉዱማሌ ፓርክ ዓመታዊ የልጆች የንባብ ፌስቲቫል ይካሄዳል። በዕለቱ በርካታ ዝግጅቶች የሚቀርቡ ሲሆን የመጽሀፍት አውደርዕይና ባዛርን ጨምሮ ሌሎች አስተማሪና አዝናኝ ዝግጅቶች ይቀርባሉ።
የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ ፓርኩን ለንባብ ክፍት መሆኑን ለማሳወቅ፣ ለተሻለች ኢትዮጵያ የተሻለ አንባቢ ትውልድ ለመገንባትና ልጆች ክረምትን በንባብ እንዲያሳልፋ ለማድረግ ያለመ ነው።
Responses