የህይወታችን መዓዛ
ማንበብ ለህይወታችን የሚሰጠው መዓዛ፣ የሚፈጥርልን ልዩ ስሜት፣ የሚያጎናፅፈን ነፃነት በቃላት ተሰፍሮ የሚያልቅ አይደለም። መፀሀፍት በየትኛውም ደብዛዛ ዘመን ጊዜን የማፍካት ጉልበት ያላቸው፤የህይወት ቅመም ናቸዉ። ማንበብ አንድ ከሚበራ ሻማ ላይ ወደ ሌላ ቁራጭ ሻማ ብርሀን ቢለኮስ፤ ሲበራ የነበረዉ ሻማ እንደማይጠፋ ሁሉ፤ አንባቢ ደግሞ ከንባቡ ያገኘውን እዉቀት በማካፈል በሌላ ሰዉ ህይወት ዉሰጥ የሚበራ ሻማ እንዲሆን ሀይልን ያቀዳጃል። እኛም ከበዛብን የስራ ጫና፣ ከሚፈታተነን የህይወት አዙሪት በተለየ መልኩ ለማሰብ እንድንችል በተጣበበ ጊዜም ቢሆን ዕለት ዕለት ጥቂት እናንብብ፣ አንብበንም ስብዕናችንን እንገንባ፣ ማንነታችንን እናስውብ። መልዕክታችን ነው።
Responses