ዕውቀት ትልቁ የምድራችን ኃይል
ኃያል ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን አትፈልጉም? _ ማንም _ የማያሸንፋችሁ፤ማንም ነቅንቆ የማይጥላችሁ፤ማንም የማያስፈራችሁ፤ብትወድቁ እንኳን የምትነሱ፤ብታለቅሱ _ እንኳን መልሳችሁ የምትስቁ፤መሠረታችሁ የጸና ከምንጩ ጀምሮ ራሳችሁን የምታውቁ ኃይለኛ
መሆን ትፈልጋላችሁ? ተናግራችሁ የምትደመጡ፣መጣብን ሳይሆን መጣልን የምትባሉ የመፍትሄ ሰው መሆን ትሻላችሁ? ሰዎች ከመቀመጫቸው የሚነሱላችሁ፣ ተጣርታችሁ የሚደርሱላችሁ፣ አዛችሁ የሚፈፀምላችሁ፣ ጠይቃችሁ የሚመለስላችሁ ተደማጭ፣ ተሰሚና ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን ከፈለጋችሁ ዕውቀትን ፈልጓት። ዕውቀት ትልቁ የምድራችን ኃይል ነው። ይህንን ልዩነት ፈጣሪ ኃይል ከጥበብ ከማስተዋልና ከድንቅ ማንነት ጋር ለመጎናፀፍ ንባብን ምርጫዎ ያድርጉ፣ መጽሃፍትን ይወዳጁ።
ኢዮብ ጽጌ
ሐምሌ 29
Responses