እናነባለን!!!!

እናነባለን!!!

ስለሚያዝናናን
ስለሚያስቀን
ስለሚያስለቅሰን
ስለሚያስደስተን
ስለሚያሳዝነን
ስለሚያወዛግበን
(ተወዛግበን ደግሞ አንቀርም,,,,
አበው በጥበባቸው
ሳይጣመም አይቃናም፤
ሳይደፈርስ አይጠራም ብለው ከመጽሀፍ አስቀምጠውልናልና!)
ህይወታችንን በዚህ ሁሉ ክቡር ስሜት ስለሚሞላልን እናነባለን።

ወደላይ ስለሚያጎነን
ወደታች ስለሚያፈርጠን
ወደኋላ ስለሚስበን
ወደፊት ስለሚገፋን
ከታሪክ ስለሚያስቃኝን
በምናብ ስለሚያንሳፈን
ለዚህ ሁሉ ስንል እናነባለን!!!

ወደ ነፍስ ስለሚያጠልቀን
ወደ አለም ስለሚያሰፋን
ከብቸኝነት ስለሚፈውሰን
ወደ ራስ ስለሚያቀርበን
ወደ ሩቅ ስለሚያስፈነጥረን
እናነባለን!!!

እንደ አባት ስለሚገስጸን
እንደጓደኛ ስለሚመክረን
እንደ ልጅ ስለሚያጫውተን
እንደወረተኛ ስለማይከዳን እናነባለን!!!

እናንተም ኑና አብረን እናንብብ!!! መጽሀፍት ለሁሉም!!!
ከቴዎድሮስ ሸዋንግዛው ገፅ የተወሰደ

Related Articles

ለዚህ ነው ማንበብ የሚያስደስተኝ፣ አንባቢ ሰው የሚያስቅቀናኝ፣ መጽሀፍት የሚያጓጉኝ!!!

አንባቢ ሰው አንባቢ ሲናገር አይደነቃቀፍም፤ ሃሳብ አይነጥፍበትም። እንዲያውም ቃላት ለሃሳቦቹ ይሰግዳሉ። ቋንቋ ይታዘዘዋል። የቃላት ሃብቱ ንግግሩ በጉጉት እንዲደመጥ ይጎተጉታሉ። አንባቢ ሰው ትልቅ የሃሳብ ጎተራ አለው።…

መጽሀፍት ክቡር ናቸው!

“የህይወታችን ትልቁ ደስታ መፀሀፍ ከማንበብ የሚገኝ ነው ብዬ በድፍረት ላውጅ እችላለሁ።ምክንያቱም መጽሐፍት ዓለምን ሁሉ የቀየሩ የስልጣኔ ዋና ቁልፎች ናቸው። ዓለም እዚህ የደረሰችው መፃሕፍት ታትመው ነው።…

ንባብ አጭር የሆነችውን ሕይወት በረጅሙ ለመኖር የሚረዳ ተመራጭ መንገድ በመሆኑመጽሀፍትን እንመርምር

መጻሕፍት የረቀቀውን አጉልትው የሚያሳዩ፣የተሰወረውን ምስጢር ገልጠው የሚያስረዱ የእውቀትና የጥበብ ምንጮች ናቸው፡፡ይህንን ዘመን-ዘለቅ እውነታ በውል የተገነዘቡት አበው ‹‹ሁሉንም መርምሩ መልካሙን ያዙ›› በማለት አበክረው ይመክራሉ፡፡በምክራቸውም የማያውቁትን በጥልቀት…

ፍቅር የያዘኝ

ባለቤቴን በጣም እወዳታለሁ፣ ለህይወቴ ትርጉም የሰጠቻት እሷ ናት። እኔ ግን ሌላ ፍቅረኛ አለችኝ።ከሷ ጋር ስሆን ባለቤቴ ደስ አይላትም፣ ጊዜዋን የምሻማበት ስለሚመስላት ግንኙነታችንን አትወደውም። እኔ ደሞ…

Responses