ንባብ አጭር የሆነችውን ሕይወት በረጅሙ ለመኖር የሚረዳ ተመራጭ መንገድ በመሆኑመጽሀፍትን እንመርምር

መጻሕፍት የረቀቀውን አጉልትው የሚያሳዩ፣የተሰወረውን ምስጢር ገልጠው የሚያስረዱ የእውቀትና የጥበብ ምንጮች ናቸው፡፡ይህንን ዘመን-ዘለቅ እውነታ በውል የተገነዘቡት አበው ‹‹ሁሉንም መርምሩ መልካሙን ያዙ›› በማለት አበክረው ይመክራሉ፡፡በምክራቸውም የማያውቁትን በጥልቀት መርምሮ፣ መልካም ያሉትን አጥብቆ የመያዝን ጠቀሜታ ይጠቁማሉ፡፡ የማያውቁትን ጠልቆ ለመመርመር፣ጠንቅቆ ለማወቅም ሆነ አጥብቆ ለመያዝ ደግሞ ከንባብ የተሻለ አማራጭ የለም፡፡ለምን ቢባል መጽሀፍትን ማንበብ ማንነትን ከስር ከመሠረቱ ለማወቅ፣አስተሳሰብን ለመቀየር፣ሕይወትን ለመለዋወጥና ባለራዕይ ለመሆን ያስችላልና ነው፡፡

በመሆኑም ዘርፈ ብዙ ጥበብን ለመገብየት የሚተጋ ማንኛውም ሰው (ዜጋ) በተለይ ደግሞ ወጣቱ ትውልድ/የመጻሕፍትን የእውቀት ማዕድ በመቋደስ አእምሮን ማጎልመስ ይጠበቅበታል፡፡ይህ ሲሆን ብቻ ነው የሕይወት ዘመን ውጥኑን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል የእውቀት አቅም መፍጠር የሚችለው፤ብሎም በእውቀት ላይ በተመሠረተ አኩሪ ተግባሩ የትውልድና የሀገር ተረካቢነት አደራውን በአግባቡ የሚወጣው፡፡ስለሆነም  የዛሬው መልዕክት ንባብ አጭር የሆነችውን ሕይወ በረጅሙ ለመኖር የሚረዳ ተመራጭ መንገድ በመሆኑመጽሀፍትን እንመርምር እላለሁ።ኢዮብ ጽጌ ታህሳስ 5

Related Articles

ንባብን ባህል እናድርግ!

ተወደደም ፣ ተጠላም እውቀት የአንድ ሀገር ህልውና ማስቀጠያ ሀዲድ ነው ። ያለ እውቀት መኖር ፣ ያለ ጥበብ መኖር ኋላ ቀር ትውልድ እንዲፈጠር ያደርጋል። አለም የተራቀቀችው…

ህይወት በማንበብ ትዋባለች፣ ታብባለች፣ ትፈካለች።

ህይወት የምትሸነፈው በትምህርት ብዛት ወይም ረቂቅ እውቀቶችን በመረዳትብቻ አይደለም። ኑሮን የተሻለ ለማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ እራስን የተሻለ አድርጎ መገኘት ነው። በአካል፣ በአስተሳሰብ፣ በስነልቦና፣ የአላማ ሰው በመሆን…

ማንበብን መውደድ ተማሩ

ማንበብን መውደድ ተማሩ፡ መጽሐፍ ማንበብ ከየትኛውም ደስታ በላይ ነው; ማንም ሰው በምድር ላይ ሊያሳልፍ ከሚገባው በጣም ከፍተኛ-ውሳኔዎችአንዱ ንባብ መውደድ ነው። ትኩረትን በሚከፋፍሉ ነገሮች በተሞላ፣በየጊዜው በሚለዋወጠው ዓለም መጻሕፍት ጊዜ የማይሽራቸው የእውቀት፣ የጥበብ እና…

Responses