ንባብ አሰላሳይ ያደርጋል
ንባብ ህሊናን አሰላሳይ ያደርጋል።
የአንባቢ ኅሊና ጽልመተ ኅሊናን ታበራለች ቁረተ ልቡናን ታግላለች፡፡አለማወቅን ያህል ደዌን ትፈውሳለች፡፡አለማወቅን ያህል በሽታ ይዞ ሰው ጤነኛ ሊባል አይችልምና፡፡ አንባቢ ሰው የሐሳብ ደም በኅሊና ልቡ ለሕዋሳቱ ይረጫል ፡፡ ሐሳብ ቅዳ አሳብ መልስ ማለት ነው!!፡፡
ጽሑፉ ለዓይናችን አሳቡ ለኅሊናችን ይሆናል፡፡ ጽጌረዳ የሚያሸት ሰው ፦አበባው ለዓይኑ፣መዓዛው ለአፈንጫው፣ፍቅሩ ለአእምሮው እንደመሚሆን፡፡ የሚያነብ ሰውም ንባቡ ለዐይኑ፣ምሥጢሩ ለልቡናው፣መዓዛ ጣዕሙ ለሕይወቱ ይሆናል፡
የሚያነብ ሰው – አለም እሱ ከሚያውቃቸው ነገሮች ባሻገር ብዙ ነገር እንዳላት ይረዳል፤,የበለጠ ለመማር ለማወቅ ዝግጁ ይሆናል፤ የልዩነት ሀሳብን መቀበልና ማክበር አይነት ነገሮች አያስቸግሩትም፤ ትክክለኛነትን በሆነ አጥር አይለካም፤ ባለመግባባት መግባባት፣ በአመለካከትም ሆነ ሌላ ልዩነት መኖር ማለት ጠላትነት ሳይሆን ልዩነት መሆኑን ይገነዘባል፤ እንዲሁም ልዩነት የመማር ምንጭ ሲያልፍም ዉበትና ጉልበት መሆኑን ይረዳል። በዚህ ክረምት መጽሀፍትን ብናነባቸው እጅጉን እናተርፋለን፡፡
Responses