ንባብ ባህል ሲሆን
የንባብ ባህል ያዳበረ ግለሰብ


* 1 -የጥበብ ምስጢር በጥልቀት የመመርመር አእምሮአዊ ብቃቱን ያሳድጋል፡፡
* 2 -ዘርፈ-ብዙ እውቀትን የመገንዘብ አቅሙን ያዳብራል፡፡
* 3 -አዳዲስ በሚወጡ እውቀቶች የአስተሳሰብ አድማሱን ያሰፋል፡፡
* 4 -ሕይወቱን በግብታዊነት ሳይሆን በምክንያት ይመራል፡፡
* 5 -በኑሮ ውጣ ውረድ የሚያጋጥሙ ችግሮችን የመፍታት አቅሙን ያዳብራል፡፡
* 6 -በእውቀቱ ልክ መጥኖ የጀመረውን የሕይወት ጉዞ ለስኬት ያበቃል፡፡
* 7 -ነገሮችን አስፍቶ ማየት ይችላል፡፤
* 8 -የተሰማራበትን ሙያ የማፍቀር ጠቀሜታን ይረዳል፡፡
* 9 -በጥድፍያ ውስጥ ባለ ማህበረሰብ ውስጥ በአሸናፊነት የመኖርን ግንዛቤ ይፈጥራል፡፡
10 -አስተሳሰቡን በመቀየር ሕይወቱን ለመለወጥ የሚያልም ባለራእይ ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ መፃሕፍት አንባቢ ስትሆን አመዛዛኝ ኅሊና ይኖርሃል :: ከግልብነት አውጥቶ ጥልቀት ይሰጥሃል። ሰዎች ፊት ቀርበህ ለመሟገት ከማንም አታንስም። አነጋገርህ ሁሉ ያማረና አንደበተ – ርቱዕ ይኾናል።
መጻሕፍት አንባቢ ከሆንክ ሌሎች በቀደዱልህ ሁሉ አትፈስም። በጥብቅ ጠያቂና መርማሪ ትሆናለህ እንጂ !
Responses