ንባብን ባህል እናድርግ!

ተወደደም ፣ ተጠላም እውቀት የአንድ ሀገር ህልውና ማስቀጠያ ሀዲድ ነው ። ያለ እውቀት መኖር ፣ ያለ ጥበብ መኖር ኋላ ቀር ትውልድ እንዲፈጠር ያደርጋል። አለም የተራቀቀችው ፣ የመሰጠረችው ፣ የተዋበችው በእውቀት ነው። እውቀት ደሞ የሚገኘው አንድም ከንባብ ነው፡፡ በማንበብ ያልዳበረ ሰው አዲስ ሀሳብ አይኖረውም፡፡
ባላነበብን ቁጥር የማሰብ አቅማችንን ያሽመድምዳል። አእምሮ ደግሞ ያለ እውቀት ሲመራ ስንፍናና ቸልተኝነት ይነግሳል። እንደ ህዝብ የሰከነ ፣ የለዘበ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የአስተሳሰብ አድማሱ የተቃኘ ፣ ሥራ ወዳድ ፣ ሀገር ወዳድ ፣ ጠያቂ ፣ መርማሪ ፣ አሰላሳይ ፣ ለሚያምነው እምነት ታማኝ የሆነ ፣ ጨዋ ማህበረሰብ ባህሉን የሚያውቅ ፣ ታሪኩን በጥንቃቄ ሚመረምር ድንቅ ትውልድ መፍጠር የውዴታ ግዴታችን ነው።
ተፅዕኖ ፈጣሪ ማንነትን ለመላበስና የተዋበ ስብዕና ባለቤት ለመሆን የንባብ ባህላችንን እናዳብር፡
ሁሉን አይነት መፅሀፍት በልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል፡፡
https://t.me/EYOBBOOKZONE

Related Articles

ንባብ አሰላሳይ ያደርጋል

ንባብ ህሊናን አሰላሳይ ያደርጋል። የአንባቢ ኅሊና ጽልመተ ኅሊናን ታበራለች ቁረተ ልቡናን ታግላለች፡፡አለማወቅን ያህል ደዌን ትፈውሳለች፡፡አለማወቅን ያህል በሽታ ይዞ ሰው ጤነኛ ሊባል አይችልምና፡፡ አንባቢ ሰው የሐሳብ…

ለዚህ ነው ማንበብ የሚያስደስተኝ፣ አንባቢ ሰው የሚያስቅቀናኝ፣ መጽሀፍት የሚያጓጉኝ!!!

አንባቢ ሰው አንባቢ ሲናገር አይደነቃቀፍም፤ ሃሳብ አይነጥፍበትም። እንዲያውም ቃላት ለሃሳቦቹ ይሰግዳሉ። ቋንቋ ይታዘዘዋል። የቃላት ሃብቱ ንግግሩ በጉጉት እንዲደመጥ ይጎተጉታሉ። አንባቢ ሰው ትልቅ የሃሳብ ጎተራ አለው።…

Responses